ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ሲራክ 49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)ንጉሡ ኢዮስያስ 1 የኢዮስያስ መታሰቢያው በቀማሚ ብልሃት እንደ ተቀመመ ሽቱ ነው፤ እንደ ማርም በአፍ ሁሉ ጣፋጭ ነው፤ በመጠጥ ግብዣም ጊዜ እንደ ዘፈን ነው። 2 እርሱ የቀና ነው፤ ሕዝቡንም መለሳቸው፤ የኀጢአትንም ርኵሰት ሁሉ አስወገደ። 3 ልቡናውንም ወደ እግዚአብሔር አቀና፤ በኃጥኣንም ዘመን ጽድቅን አጸናት። 4 ከዳዊት፥ ከሕዝቅያስና ከኢዮስያስ በቀር ሁሉም በድለዋል፤ የልዑልን ሕግ ትተዋልና፤ የይሁዳም ነገሥታት አለቁ። 5 ኀይላቸውን ለሌላ ሰጥተዋልና፥ ክብራቸውንም ለሌላ ሕዝብ ሰጥተዋልና። ነቢዩ ኤርምያስ 6 የተመረጠችውንና የተቀደሰችውን ከተማ አቃጠሏት። መከራ አጽንተውባታልና እንደ ነቢዩ ኤርምያስ ትንቢት ጎዳናዋን አጠፉ። 7 አሠቃይተውታልና፤ እርሱ ግን ነቢይ ይሆን ዘንድ፥ ይነቅል ዘንድ፥ ያጠፋም ዘንድ፥ እንደዚሁም ይተክል ዘንድ፥ ይሠራም ዘንድ በእናቱ ማኅፀን ተመረጠ። ነቢዩ ሕዝቅኤል 8 ሕዝቅኤልም የጌትነቱን ራእይ አየ፥ እግዚአብሔርንም በኪሩቤል ሠረገላ ላይ አየው። 9 ጠላቶቹንም በመዓት ዐሰባቸው፥ የጻድቃንንም ጎዳናቸውን በመልካም አቀና። 10 የዐሥራ ሁለቱ ነቢያትም አጽሞቻቸው በየቦታቸው ለመለሙ፤ ያዕቆብን አጽናንተውታልና፥ በታመነ ተስፋም አድነውታልና። 11 ዘሩባቤልን እንዴት እናገንነው ይሆን! እርሱስ በቀኝ እጅ እንዳለ እንደ ሐቲም ቀለበት ነው። 12 የዮሴዴቅ ልጅ ዮሴዕም እንዲሁ ነበረ፤ በዘመናቸውም ቤተ መቅደስን ሠሩ፤ ለዘለዓለም ክብር የተዘጋጀ የእግዚአብሔርንም ሕዝብ አከበሩት። 13 የነሕምያም መታሰቢያው ብዙ ነው፤ የወደቀችውን ቅጽር አነሣልን፤ ደጃፎችንም አቆመልን፤ ቍልፍንም ሠራልን፥ ቤታችንንም ገነባልን። 14 እንደ ሄኖክ ያለ ሰው በምድር የተፈጠረ የለም፤ እርሱ ከዚህ ዓለም ተወሰደ። 15 እንደ ዮሴፍም ያለ ሰው አልተወለደም፤ ለወንድሞቹ አለቃ ሆነ፤ ለሕዝቡም ኀይል ሆነ፥ ለአጽሞቹም ይቅርታን አገኘ። 16 ሴምና ሴት ከሰው ይልቅ ከበሩ፥ አዳምም ከተፈጠረው ሕያው ፍጥረት ሁሉ ከበረ፤ |