የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች

መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን


መጽ​ሐፈ ጦቢት 14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽ​ሐፈ ጦቢት 14

የጦ​ቢት የመ​ጨ​ረሻ ምክር

1 ከዚህ በኋላ ጦቢት ከመ​ጸ​ለይ ዝም አለ፤

2 ዐይ​ኑም በጠፋ ጊዜ አምሳ ስም​ንት ዓመት ሆኖት ነበር። ከስ​ም​ንት ዓመት በኋ​ላም አየ፤ ምጽ​ዋ​ትም መጸ​ወተ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራ​ት​ንም ጨመረ፤ በእ​ር​ሱም አመነ።

3 ፈጽሞ አረጀ፤ ልጁ​ንና የል​ጁ​ንም ልጆች ጠራ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “አር​ጅ​ቻ​ለ​ሁና፥ ለሞ​ትም ደር​ሻ​ለ​ሁና ልጆ​ች​ህን አም​ጣ​ቸው።”

4 ልጄ፥ ወደ ሜዶን ሂድ፤ ትጠፋ ዘንድ እን​ዳ​ላት ነቢዩ ዮናስ በነ​ነዌ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ነገር ሁሉ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ በሜ​ዶን ግን እስከ ዘመኑ ድረስ ሰላም ይሆ​ናል። ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ከተ​ባ​ረ​ከች ምድር ሁሉ ወደ​የ​ሀ​ገሩ ይበ​ተኑ ዘንድ አላ​ቸው፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ምድረ በዳ ትሆ​ና​ለች፤ በእ​ር​ስ​ዋም ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይቃ​ጠ​ላል፤ እስከ ዘመ​ኑም ድረስ ምድረ በዳ ይሆ​ናል።

5 ዳግ​መ​ኛም እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር ይቅር ብሎ ወደ ሀገ​ራ​ቸው ይመ​ል​ሳ​ቸ​ዋል፤ ማደ​ሪ​ያው ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም ይሠ​ራሉ፤ የዘ​መኑ ቍጥር እስ​ከ​ሚ​ፈ​ጸም ነው እንጂ እንደ ቀድ​ሞው አይ​ደ​ለም፤ ከዚ​ህም በኋላ ከተ​ማ​ረ​ኩ​በት ይመ​ለ​ሳሉ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በክ​ብር ይሠ​ሯ​ታል፤ በእ​ር​ሷም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት እስከ ልጅ ልጅ ዘመን ድረስ በዕ​ብነ በረድ ይሠ​ራሉ።

6 አሕ​ዛ​ብም ሁሉ በእ​ው​ነት ወደ እርሱ ይመ​ለ​ሳሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ይፈ​ሩ​ታል፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጥ​ላሉ።

7 አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል። ሕዝ​ቡም በእ​ርሱ ያም​ናሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወገ​ኖ​ቹን ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል። በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ ሰዎች ሁሉ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ቸር​ነ​ትን ያደ​ር​ጋሉ።

8 “ልጄ ሆይ! አሁ​ንም ከነ​ነዌ ውጣ፤ ነቢዩ ዮናስ የተ​ና​ገ​ረው ነገር በግድ ይደ​ረ​ጋ​ልና።

9 አንተ ግን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሕጉን ጠብቅ፤ ይቅር ባይም ሁን፤ በጎ ይደ​ረ​ግ​ልህ ዘንድ እው​ነ​ትን ውደድ።

10 አክ​ብ​ረህ ቅበ​ረኝ፤ እና​ት​ህ​ንም ከእኔ ጋር ቅበ​ራት። ልጄ፥ በነ​ነዌ አት​ቈይ። ሐማ በዘ​መ​ድህ በአ​ኪ​አ​ክ​ሮስ ያደ​ረ​ገ​ውን፥ ከብ​ር​ሃን ወደ ጨለማ እን​ዳ​ገ​ባው፥ ፍዳ​ው​ንም እንደ ተቀ​በለ፥ አኪ​አ​ክ​ሮ​ስም እንደ ዳነ እይ። እርሱ ግን ፍዳ​ውን ተቀ​በለ፤ እርሱ ወደ ጨለማ ወረደ። ምናሴ ምጽ​ዋ​ትን አደ​ረገ፤ እው​ነ​ት​ንም አደ​ረገ፤ ከመ​ከ​ሩ​በት ከሞት መቅ​ሠ​ፍ​ትም ዳነ። ሐማ ግን በዚ​ያች ወጥ​መድ ወደ​ቀና ሞተ።

የጦ​ቢ​ትና የሚ​ስቱ ሞት

11 “አሁ​ንም ልጄ፥ ምጽ​ዋት የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን እይ፤ ከሞት ታድ​ና​ለች፤ ታጸ​ድ​ቃ​ለ​ችም።” ጦቢ​ትም ይህን ተና​ግሮ ሞተ፤ ባል​ጋው ላይ ሳለም ነፍሱ ከሥ​ጋው ተለ​የች። መቶ አምሳ ስም​ንት ዐመ​ትም ሆኖት ነበር። በክ​ብ​ርም ቀበ​ሩት፤

12 እናቱ ሐናም በሞ​ተች ጊዜ ካባቱ ጋራ ቀበ​ራት። ጦብ​ያም ከሚ​ስ​ቱና ከል​ጆቹ ጋር አማቱ ራጉ​ኤል ወዳ​ለ​በት ወደ ባጥና ሄደ።

13 ራጉ​ኤ​ልና ሚስቱ አድ​ናም አር​ጅ​ተው ሞቱ። አማ​ቶ​ቹ​ንም አክ​ብሮ ቀበ​ራ​ቸው። ገን​ዘ​ባ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ወረሰ። የአ​ባ​ቱን የጦ​ቢ​ትን ገን​ዘ​ብም ወረሰ።

14 ጦብ​ያም በመቶ ሃያ ሰባት ዓመቱ ሞተ፤ የሜ​ዶን ክፍል በም​ት​ሆን በባ​ጥ​ናም ተቀ​በረ።

15 አባ​ቱም እንደ ነገ​ረው ሳይ​ሞት የነ​ነ​ዌን ጥፋት ሰማ። ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና አሕ​ሻ​ዊ​ሮ​ስም የነ​ነ​ዌን ጥፋት ሰም​ተው ደስ አላ​ቸው። የጦ​ቢ​ትና የልጁ የጦ​ብያ ነገር ተፈ​ጸመ። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ክብር ምስ​ጋና ይግ​ባው አሜን።