Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽ​ሐፈ ጦቢት 13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ጦቢት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረ​በው ምስ​ጋና

1 ጦቢ​ትም የደ​ስታ መጽ​ሐ​ፍን ጻፈ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ ሕያው የሚ​ሆን፥ መን​ግ​ሥ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ የሆነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን።

2 እርሱ ይገ​ር​ፋል፤ ይቅ​ርም ይላል፤ እርሱ ወደ ሲኦል ያወ​ር​ዳል፤ ያወ​ጣ​ልም፤ ከእ​ጁም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም።

3 እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ እርሱ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በበ​ተ​ነን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ተገ​ዙ​ለት።

4 በዚ​ያም ገና​ና​ነ​ቱን ገለ​ጠ​ላ​ችሁ፤ በሰው ሁሉ ፊትም አክ​ብ​ሩት፤ እርሱ ጌታ​ችን ነውና፥ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዐ​ለም አባ​ታ​ችን ነውና።

5 በኀ​ጢ​አ​ታ​ችን ይገ​ር​ፈ​ናል፤ ዳግ​መ​ኛም ይቅር ይለ​ናል፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ከበ​ተ​ነን ከአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይሰ​በ​ስ​በ​ናል።

6 “በፊቱ እው​ነ​ትን ትሠሩ ዘንድ በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ች​ሁም ወደ እርሱ ከተ​መ​ለ​ሳ​ችሁ ያን ጊዜ እርሱ ወደ እና​ንተ ይመ​ለ​ሳል። ፊቱ​ንም ከእ​ና​ንተ አይ​ሰ​ው​ርም። ከእ​ና​ንተ ጋር ያደ​ረ​ገ​ውን ታያ​ላ​ችሁ። በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ች​ሁም እመ​ኑ​በት፤ ጻድቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ንጉሥ በተ​ማ​ረ​ካ​ች​ሁ​በት ሀገር ከፍ ከፍ አድ​ር​ጉት፤ እኔም በተ​ማ​ረ​ክ​ሁ​በት ሀገር አም​ን​በ​ታ​ለሁ፤ ኀጢ​አ​ተ​ኞች ለሆኑ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ኀይ​ሉ​ንና ገና​ና​ነ​ቱን እና​ገ​ራ​ለሁ። እና​ንተ ኀጢ​አ​ተ​ኞች፥ ተመ​ል​ሳ​ችሁ በፊቱ እው​ነ​ትን ሥሯት፤ ወድ​ዶም ቸር​ነ​ቱን ለእ​ና​ንተ ያደ​ር​ግ​ላ​ችሁ እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል?

7 ፈጣ​ሪ​ዬን ከፍ ከፍ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ። ሰው​ነ​ቴም የሰ​ማ​ይን ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች።

8 ገና​ና​ነ​ቱ​ንም በሁሉ ዘንድ እና​ገ​ራ​ለሁ።

9 “ቅድ​ስት ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ በል​ጆ​ችሽ ኀጢ​አት በመ​ከራ አይ​ቀ​ሥ​ፍ​ሽ​ምን? ዳግ​መ​ኛም ደጋግ ለሆኑ ልጆ​ችሽ ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋል።

10 በበጎ ሥራ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገዢ፤ ባን​ቺም ዘንድ ድን​ኳኑ በደ​ስታ እን​ድ​ት​ሠራ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙን ንጉሥ አመ​ስ​ግኚ፤ በዚ​ያም ያሉ የተ​ማ​ረኩ ሰዎች ደስ ይላ​ቸ​ዋል። በዘ​ለ​ዓ​ለ​ማዊ ትው​ል​ድም ሁሉ የተ​ጠሉ በአ​ንቺ ምክ​ን​ያት ይወ​ደ​ዳሉ።

11 “ብዙ አሕ​ዛብ ከሩቅ ወደ ፈጣሪ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ይመ​ጣሉ፤ ለሰ​ማይ ንጉ​ሥም እጅ መን​ሻን ያመ​ጣሉ፥ ትው​ል​ድም ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ሃል፤ ለስ​ም​ህም ምስ​ጋ​ናን ያቀ​ር​ባሉ።

12 የሚ​ጠ​ሉህ ሁሉ የተ​ረ​ገሙ ናቸው፤ የሚ​ወ​ድ​ዱህ ሁሉ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ የተ​ባ​ረኩ ናቸው።

13 በጻ​ድ​ቃን ልጆች ደስ ይል​ሃል፤ አቤቱ፥ በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው የጻ​ድ​ቃ​ንን ጌታ አን​ተን ያመ​ሰ​ግ​ና​ሉና፥ የሚ​ወ​ድ​ዱህ ብፁ​ዓን ናቸ​ውና፤ በሰ​ላ​ም​ህም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።

14 ስለ መከ​ራህ የሚ​ያ​ዝኑ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው፤ ክብ​ር​ህን ሁሉ አይ​ተው በአ​ንተ ደስ ይላ​ቸ​ዋ​ልና፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ደስ ይላ​ቸ​ዋል።

15 “ሰው​ነቴ ገናና ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች።

16 ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰን​ፔር በሚ​ባል ዕንቍ ትሠ​ራ​ለ​ችና፥ ግድ​ግ​ዳዋ በመ​ረ​ግ​ድና በከ​በረ ዕንቍ፥ አዳ​ራ​ሽ​ዋና በሮ​ችዋ በጠራ ወርቅ ይሠ​ራ​ሉና።

17 የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባ​ይም በቢ​ሬሌ፥ በአ​ት​ራ​ኮስ ዕን​ቍና በሶ​ፎር ዕንቍ ይሠ​ራ​ልና።

18 በጎ​ዳ​ናዋ ሁሉ ሃሌ ሉያ ይላሉ፤ እያ​መ​ሰ​ገ​ኑም እን​ዲህ ይላሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ይመ​ስ​ገን።”

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች