Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽሐፈ ሲራክ 45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ሙሴ

1 ሙሴም ስም አጠ​ራሩ የተ​ባ​ረከ ነው፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውና አም​ሳ​ሉም እንደ ቅዱ​ሳን ክብር ነው።

2 ከፍ ከፍም አደ​ረ​ገው፤ በጠ​ላ​ቶ​ቹም ላይ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ሆነ።

3 በቃ​ሉም ተአ​ም​ራ​ትን አደ​ረገ፤ በነ​ገ​ሥ​ታ​ቱም ፊት አከ​በ​ረው፤ ስለ ሕዝ​ቡም አዘ​ዘው፤ ክብ​ሩ​ንም አሳ​የው።

4 ስለ ሃይ​ማ​ኖ​ቱና ስለ የዋ​ህ​ነ​ቱም ቀደ​ሰው፤ ከሰ​ውም ሁሉ እር​ሱን መረ​ጠው።

5 ቃሉ​ንም አሰ​ማው፤ ወደ ደመ​ና​ውም ውስጥ አገ​ባው፤ ትእ​ዛ​ዙ​ንም በፊቱ ሰጠው፤ ለያ​ዕ​ቆብ ቃል ኪዳ​ኑን፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ፍር​ዱን ያስ​ተ​ምር ዘንድ የሕ​ይ​ወት ሕግን ሰጠው።


አሮን

6 ከሌዊ ወገን የተ​ወ​ለደ ወን​ድሙ አሮ​ንም እንደ እርሱ ታላቅ ነው፤ ቅዱ​ስም፥ የከ​በ​ረም ነው።

7 የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ​ንም አጸ​ና​ለት፤ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ክህ​ነ​ትን ሰጠው፤ በአ​ማረ ጌጥም አስ​ደ​ነ​ቀው፤ የክ​ብር ልብ​ስ​ንም አለ​በ​ሰው።

8 በሁ​ሉም ዘንድ አስ​መ​ካው፤ በከ​በሩ ልብ​ሶ​ችም አጸ​ናው፤ እጀ ሰፊና እጀ ጠባ​ብ​ንም፥ ኤፉ​ድ​ንም አለ​በ​ሰው።

9 በዙ​ሪ​ያ​ውም ብዙ ሮማ​ንና የወ​ርቅ ጸና​ጽል አለ፤ በእ​ግ​ሩም በረ​ገጠ ጊዜ የመ​ር​ገፉ ድምፅ በቤተ መቅ​ደስ ይሰማ ዘንድ ይጮህ ነበር፤ ይህም ለሕ​ዝ​ቡና ለል​ጆ​ቻ​ቸው መታ​ሰ​ቢያ ሆነ።

10 የተ​ለየ ሰማ​ያዊ ሐር ያለ​በት አራት ኅብ​ርን፥ አም​ስ​ተኛ ወርቀ ዘቦ ያለ​በት በነጭ ሐር የተ​ሠራ ልብ​ስ​ንም፥ በሚ​ገ​ባና በእ​ው​ነት ነገር የተ​ሠራ ልብሰ መት​ከፍ አለ​በ​ሰው።

11 የነጭ ሐር የሚ​ሆን ፈትሉ እጥፍ የሆነ፥ ዕን​ቍም ያለ​በት፥ የማ​ኅ​ተ​ምም ቅርጽ ያለ​በት ልብ​ስን በል​ብስ ላይ አለ​በ​ሰው፤ እጀ ጠባ​ቡም በወ​ርቅ የተ​ሠራ ነው፤ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው መታ​ሰ​ቢያ ሊሆን በዐ​ሥራ ሁለቱ ነገደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ቍጥር ልክ የተ​ጻፈ ነው።

12 በማ​ኅ​ተም መልክ አም​ሳል የተ​ሠራ የወ​ርቅ አክ​ሊ​ልን በዝ​ግራ መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያው ላይ አደ​ረ​ገ​ለት፤ የተ​ለየ የክ​ብሩ መመ​ኪያ የሚ​ሆን ተአ​ም​ራት የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​በት፥ ለዐ​ይን የተ​ወ​ደደ፥ ጌጡ ፈጽሞ ያማረ የወ​ርቅ መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያን በዝ​ግራ መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያው ላይ አደ​ረ​ገ​ለት።

13 ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ እንደ እርሱ ልብስ ያለ ልብስ አል​ተ​ሠ​ራም፤ ከል​ጆቹ ብቻ በቀር፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ከዘ​መ​ዶ​ቹም በቀር እንደ እርሱ የለ​በሰ የለም።

14 ሁል​ጊዜ በየ​ዕ​ለቱ የጧ​ትና የማታ መሥ​ዋ​ዕት ይሠ​ዉ​ለት ዘንድ፥

15 ሙሴም እጃ​ቸ​ውን ቀባ​ላ​ቸው፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ዘይት ቀባው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ሕግ ሆነው፤ ይገ​ዙ​ለት ዘንድ፤ ካህ​ና​ትም ይሆ​ኑት ዘንድ፤ ሕዝ​ቡ​ንም በስሙ ይባ​ር​ኳ​ቸው ዘንድ፤ ሰማይ ጸንቶ በሚ​ኖ​ር​በት ዘመን ልክ ለል​ጆቹ ሕግ ሆና​ቸው።

16 ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት ይሠዋ ዘንድ፥ የበጎ መዓዛ መታ​ሰ​ቢ​ያም ሊሆን ዕጣ​ንን ያጥን ዘንድ፥ ለሕ​ዝ​ቡም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ቸው ዘንድ ከሕ​ያ​ዋን ሁሉ እር​ሱን መረጠ።

17 ትእ​ዛ​ዛ​ቱን ሰጠው፤ ለያ​ዕ​ቆብ ምስ​ክ​ሩን ያስ​ተ​ም​ረው፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕጉን ያስ​ተ​ም​ረው ዘንድ ፍር​ድ​ንና ሥል​ጣ​ንን ሰጠው።

18 ሌሎች ግን ተቃ​ወ​ሙት፤ የዳ​ታ​ንና የአ​ቤ​ሮን የሆኑ ሰዎች፥ የእ​ነ​ቆ​ሬም ሠራ​ዊት በመ​ና​ደ​ድና በመ​ቈ​ጣት በም​ድረ በዳ ቀኑ​በት።

19 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አያ​ቸው፤ ደስም አላ​ሰ​ኙ​ትም፤ ተቈ​ጥ​ቶም አጠ​ፋ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ድንቅ ተአ​ም​ራ​ትን አደ​ረገ፤ በእ​ሳ​ትም አጠ​ፋ​ቸው።

20 ለአ​ሮ​ንም ክብ​ርን ጨመ​ረ​ለት፤ የእ​ህ​ላ​ቸ​ው​ንም ቀዳ​ም​ያት ዕድል ፋንታ አድ​ርጎ ሰጠው።

21 ለእ​ር​ሱና ለል​ጆ​ቹም የሰ​ጣ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሥ​ዋ​ዕት ይበሉ ዘንድ፥ የሚ​ያ​ጠ​ግ​ባ​ቸው ዐሥ​ራ​ቱን አስ​ቀ​ድሞ ሠራ​ላ​ቸው።

22 የሕ​ዝ​ቡ​ንም ምድር አል​ተ​ካ​ፈ​ለም፤ ከሕ​ዝ​ቡም ጋራ ርስ​ትን አል​ወ​ረ​ሰም፤ እርሱ ራሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዕድሉ፥ ርስ​ቱም ነውና።


ፊን​ሐስ

23 የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐ​ስም በክ​ብር ሦስ​ተኛ ነው፤ ለአ​ም​ል​ኮተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን​ቶ​አ​ልና፥ ሕዝ​ቡ​ንም ለማ​ስ​ተ​ማር አስ​ነ​ሥ​ቶ​ታ​ልና፥ በል​ቡ​ናው ቸር​ነ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ የተ​ነሣ ለእ​ስ​ራ​ኤል አስ​ተ​ሰ​ረየ።

24 ስለ​ዚ​ህም ለሕ​ዝቡ የቅ​ዱ​ሳ​ንን ሥር​ዐት ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ዘንድ፥ ለእ​ር​ሱና ለዘ​ሩም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ደገኛ ክህ​ነት ይሆን ዘንድ የሰ​ላም ኪዳ​ንን አጸ​ና​ለት።

25 ከነ​ገደ ይሁዳ ለተ​ወ​ለደ ለዳ​ዊት ልጅም ጌጥ ይሆን ዘንድ፥ በሕጉ ጸንቶ የሚ​ኖር የልጁ መን​ግ​ሥ​ትም እድል ይሆን ዘንድ፤

26 በል​ቡ​ና​ቸ​ውም ጥበ​ብን ያሳ​ድ​ር​ባ​ቸው ዘንድ፥ በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ ክብ​ራ​ቸ​ውና በረ​ከ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ጠ​ፋ​ባ​ቸው፥ ወገ​ኖ​ቹ​ንም በእ​ው​ነት ይገ​ዟ​ቸው ዘንድ ከል​ጆቹ ጋራ ለእ​ርሱ ክህ​ነት ርስቱ ነው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos