La Biblia Online

Anuncios

Toda la Biblia A.T. N.T.


መጽ​ሐፈ ዕዝራ ሱቱ​ኤል 4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽ​ሐፈ ዕዝራ ሱቱ​ኤል 4

1 እር​ሱም አለኝ፥ “መጀ​መ​ሪያ በሰው ልጅ ነው፤ በኋላ ግን እኔ ራሴ ነኝ፤ ሰማ​ይና ምድር፥ ሀገ​ሮ​ችም ሳይ​ፈ​ጠሩ፥ የዓ​ለም መን​ገ​ድም ሳይ​ጸና፥ ነፋ​ሳ​ትም ሳይ​ነ​ፍሱ፤

2 የነ​ጐ​ድ​ጓድ ድም​ፅም ሳይ​ሰማ፥ የመ​ብ​ረቅ ብል​ጭ​ታም ሳይ​በራ፥ የገ​ነት ምድር ሳይ​ፈ​ጠር፥

3 የአ​በ​ቦ​ችም ውበት ሳይ​ታይ፥ የመ​ሬት መነ​ዋ​ወጥ ኀይ​ልም ሳይ​ጸና፥ የመ​ላ​እ​ክ​ትም ሠራ​ዊት ሳይ​ቈ​ጠሩ።

4 የሰ​ማ​ይም ምጥ​ቀቱ ሳይ​ታይ፥ የሰ​ማ​ያ​ትም መስ​ፈ​ርት ሳይ​ሰ​ፈር፥

5 የሚ​መ​ጣው ዓለም ፍለጋ ሳይ​ታ​ወቅ፥ የኃ​ጥ​ኣን ጥላ ሳይ​ወ​ገድ፦ የጌታ ማኅ​ተም ሕግን በሚ​ጠ​ብ​ቁና ሃይ​ማ​ኖ​ትን በሚ​ያ​ምኑ ላይ ሳይ​ታ​ተም፥

6 ያን​ጊዜ እኔ ራሴ ይህን ዓለም እጐ​በኝ ዘንድ አሰ​ብሁ፤ ሌላም አይ​ደ​ለም።”

7 መል​ሼም እን​ዲህ አል​ሁት፥ “የመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓለም ምል​ክቱ፥ ጊዜ​ውስ ምን​ድን ነው? ፍጻ​ሜ​ውስ መቼ ነው? የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውስ ዓለም መጀ​መ​ሪ​ያው መቼ ነው?”

8 እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ከአ​ብ​ር​ሃም እስከ ይስ​ሐቅ ነው፤ ያዕ​ቆ​ብና ዔሳው ከእ​ርሱ ተወ​ል​ደ​ዋል፥ በተ​ወ​ለ​ዱም ጊዜ ያዕ​ቆብ የኤ​ሳ​ውን ተረ​ከዝ ይዞ ተወ​ለደ።

9 ኤሳው የዚህ ዘመን ፍጻሜ ምሳሌ ነው፤ ያዕ​ቆ​ብም የአ​ዲሱ ዘመን መጀ​መ​ሪያ ነው።

10 የሰው መጨ​ረሻ አካሉ ተረ​ከዙ ነውና፤ የሰ​ውም መጀ​መ​ሪያ አካሉ እጁ ነው። ነገር ግን ዕዝራ አት​መ​ራ​መር።”

11 እኔም መለ​ስ​ሁ​ለት እን​ዲ​ህም አል​ሁት፥ “አቤቱ ጌታዬ፥ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ፊት ባለ​ሟ​ል​ነ​ት​ንስ ካገ​ኘሁ፥

12 ባለ​ፈው ሌሊት አስ​ቀ​ድሞ በከ​ፊል የነ​ገ​ር​ኸ​ኝን የዚ​ህን ምል​ክት መጨ​ረሻ ለባ​ሪ​ያህ ንገ​ረው።”

13 እር​ሱም መለ​ሰ​ልኝ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ተነ​ሥ​ተህ በእ​ግ​ርህ ቁም፤ ጩኸት የተ​መ​ላ​በ​ት​ንም ቃል እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።

14 አንተ በው​ስጡ የቆ​ም​ህ​በት ቦታ ቢነ​ዋ​ወጥ በነ​ገ​ር​ሁህ ጊዜ አት​ደ​ን​ግጥ፤ ስለ ነገር መጨ​ረሻ ነውና።

15 ያን​ጊዜ የም​ድር መሠ​ረ​ቶች ነገ​ርን ያስ​ረ​ዳሉ።

16 ነገሩ ስለ እነ​ርሱ ነውና፥ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ይነ​ዋ​ወ​ጣ​ሉም፤ በመ​ጨ​ረ​ሻ​ቸው ያልፉ ዘንድ አላ​ቸ​ውና፥”

17 ከዚ​ህም በኋላ ይህን በሰ​ማሁ ጊዜ ተነ​ሥቼ በእ​ግ​ሮች ቆምሁ፤ እነሆ፥ የሚ​ና​ገ​ረ​ው​ንም ቃል ሰማሁ፤ ድም​ፁም እንደ ብዙ ውኃ ድምፅ ነበር።

18 በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ይጐ​በ​ኛ​ቸው ዘንድ ልዑል በደ​ረሰ ጊዜ እነሆ፥ ዘመን ይመ​ጣል ይል ነበር።

19 ጽዮን በታ​ነ​ጸች ጊዜ ያመ​ፁ​ብ​ኝን ዐመ​ፃ​ቸ​ውን ያን​ጊዜ እመ​ራ​መ​ራ​ቸው ዘንድ አለኝ።

20 ይመጣ ዘንድ ያለው ዓለም በታ​ተመ ጊዜ የማ​ደ​ር​ገው ምል​ክት ይህ ነው፤ በሰ​ማይ መጻ​ሕ​ፍት ይገ​ለ​ጣሉ፤ ሁሉም ያየ​ኛል።

21 ዓመት የሆ​ና​ቸው ሕፃ​ናት ፈጽ​መው ይና​ገ​ራሉ፤ የፀ​ነሱ ሴቶ​ችም የሦ​ስት ወርና የአ​ራት ወር ሕፃ​ና​ትን ይወ​ል​ዳሉ፤ ሕያ​ዋ​ንም ሆነው ይነ​ሣሉ።

22 የማ​ት​ታይ ምድ​ርም ዘርዕ ተዘ​ር​ቶ​ባት ትታ​ያ​ለች፥ ውስ​ጣ​ቸው ሙሉ የነ​በሩ ቤቶ​ችም ባዷ​ቸ​ውን ይገ​ኛሉ።

23 ነጋ​ሪት ይሰ​ማል፤ የሰ​ማ​ውም ሁሉ ይደ​ነ​ግ​ጣል።

24 በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት ወዳ​ጆች ከወ​ዳ​ጆ​ቻ​ቸው ጋር እርስ በር​ሳ​ቸው እንደ ጠላት ይዋ​ጋሉ። ምድ​ርም በው​ስጧ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትን ታስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋ​ለች፤ የው​ኃው ምን​ጮ​ችም ይገ​ታሉ፤ እስከ ሦስት ሰዓ​ትም ድረስ አይ​ፈ​ስ​ሱም።

25 “ከዚህ ከነ​ገ​ር​ሁህ ሁሉ የቀረ ሰው ሁሉ የሚ​ድን እርሱ ነው፤ ትድ​ግ​ና​ዬን የዘ​መ​ኔ​ንም ፍጻሜ የሚ​ያይ እርሱ ነው።

26 ያን​ጊ​ዜም ያረ​ጉና ከተ​ወ​ለዱ ጅምሮ ሞትን ያል​ቀ​መሱ እነ​ዚ​ያን ሰዎች ያዩ​አ​ቸ​ዋል፤ በዓ​ለም የሚ​ኖሩ ሰዎ​ችም ልቡና ይለ​ወ​ጣል፤ ሌላ ልቡ​ናም ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።

27 ክፋት ትደ​መ​ሰ​ሳ​ለ​ችና፥ ተን​ኰ​ልም ትጠ​ፋ​ለ​ችና።

28 ሃይ​ማ​ኖት ትለ​መ​ል​ማ​ለች፤ ሞት ድል ይነ​ሣል፤ ያለ ፍሬ ለብዙ ዘመን የነ​በ​ረች ጽድቅ ትገ​ለ​ጣ​ለች።”

29 በተ​ና​ገ​ረ​ኝም ጊዜ እኔ የቆ​ም​ሁ​በት ስፍራ ጥቂት ጥቂት እያለ ይነ​ዋ​ወጥ ነበር።

30 እር​ሱም አለኝ፥ “ባለ​ፈ​ችው ሌሊት እንደ ነገ​ር​ሁህ ይህን ምል​ክት እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።

31 ዳግ​መኛ ሰባት ቀን ብት​ጾ​ምና ብት​ጸ​ልይ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ዳግ​መኛ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።

32 ቃልህ በል​ዑል ዘንድ መሰ​ማ​ትን ተሰ​ም​ት​ዋ​ልና። ከሕ​ፃ​ን​ነ​ት​ህም ጀምሮ ያለው የጽ​ድ​ቅህ ኀይል ተገ​ል​ጧ​ልና።

33 ስለ​ዚ​ህም ይህን ነገር እነ​ግ​ርህ ዘንድ ልዑል ላከኝ።

34 እን​ዲ​ህም አለኝ፦ እመን፤ አት​ፍራ፤ በኋላ ዘመን እን​ዳ​ት​ጠ​ራ​ጠር ስለ ቀደ​መ​ውም ክፉ አሳ​ብህ አት​ቸ​ኩል።”

ሦስ​ተ​ኛው ራእይ

35 ከዚ​ህም በኋላ የነ​ገ​ረ​ኝን ሦስ​ቱን ሱባ​ዔ​ያት እጨ​ርስ ዘንድ ዳግ​መኛ ሰባት ቀን እያ​ለ​ቀ​ስሁ ጾምሁ።

36 በዚ​ያች ሌሊት ልቤ ታወ​ከ​ች​ብኝ፤ በል​ዑ​ልም ፊት እና​ገር ጀመ​ርሁ።

37 ሰው​ነቴ ፈጽማ ትና​ደ​ዳ​ለ​ችና፥ ልቡ​ና​ዬም ትና​ወ​ጣ​ለ​ችና።

38 እን​ዲ​ህም አልሁ፥ “አቤቱ ጌታዬ፥ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው መፍ​ጠ​ርህ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪቱ ቀን ሰማ​ይና ምድር ይፈ​ጠር አልህ፤ እን​ዲ​ሁም ተፈ​ጠረ፤ ቃል​ህም ፍጥ​ረ​ትን ይፈ​ጥር ነበር።

39 መን​ፈ​ስም ይሰ​ፍፍ ነበር። ጨለ​ማም ሞልቶ ነበር፥ ፀጥ ብሎም ነበር። ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሰው ልጅ ድምፅ ገና አል​ነ​በ​ረ​ምና።

40 ያን​ጊ​ዜም ብር​ሃን ከአ​ዳ​ራ​ሽህ እን​ዲ​ገኝ ፍጥ​ረ​ት​ህም እን​ዲ​ገ​ለጥ አዘ​ዝህ።

41 “ዳግ​መ​ኛም በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን በሰ​ማ​ያት ያለ ነፋ​ስን ፈጠ​ርህ፤ እኩ​ሌ​ታ​ውም ወደ ላይ ይወጣ ዘንድ፥ እኩ​ሌ​ታ​ውም በታች ይኖር ዘንድ በው​ኃው መካ​ከል እን​ዲ​ለይ አዘ​ዝ​ኸው።

42 ዳግ​መ​ኛም በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ውኃ​ውን ከም​ድር በሰ​ባ​ተ​ኛው እጅ ላይ እን​ዲ​ሰ​በ​ሰብ አዘ​ዝ​ኸው። የም​ድር ስድ​ስቱ እጅም በው​ስ​ጣ​ቸው ያርሱ ዘንድ፥ ዘርም ይዘሩ ዘንድ፥ በፊ​ት​ህም ይኖሩ ዘንድ ደረቅ ሆኖ ይቅር አልህ።

43 ቃል​ህም በወጣ ጊዜ ፍጥ​ረት ይፈ​ጠር ነበር።

44 ያን​ጊ​ዜም ቍጥር የሌ​ለው ብዙ ፍሬ በቀለ፤ የሁ​ሉም ጣዕሙ፥ ያበ​ባ​ውም መልክ ልዩ ልዩ ነበር፤ የእ​ን​ጨ​ቱም ዓይ​ነት ልዩ ልዩ ነበር፤ መዓ​ዛ​ውም ልዩ ልዩ ነበር።

45 “ባራ​ተ​ኛ​ይ​ቱም ቀን ያበሩ ዘንድ የጨ​ረ​ቃና የፀ​ሐይ ብር​ሃን፥ የከ​ዋ​ክ​ብ​ትም ሥር​ዐት ይፈ​ጠር ዘንድ አዘ​ዝህ።

46 ይፈ​ጠር ዘንድ ላለው ሰውም ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ አዘ​ዝ​ሃ​ቸው።

47 “ባም​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን የና​ጌብ ውኃ ያለ​በ​ትን ያን ሰባ​ተ​ኛ​ውን እጅ ሕይ​ወት ያላ​ቸ​ውን ወፎ​ች​ንና ዓሣ​ዎ​ችን ያስ​ገኝ ዘንድ አዘ​ዝ​ኸው።

48 ስለ​ዚህ ትው​ልድ ሁሉ ጌት​ነ​ት​ህን ይና​ገሩ ዘንድ የማ​ይ​ና​ገ​ርና ደመ ነፍስ የሌ​ለው ያ ውኃ ሕይ​ወት ያለ​ውን አስ​ገኘ።

49 ያን​ጊ​ዜም የፈ​ጠ​ር​ሃ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን እን​ስ​ሳት ጠበ​ቅህ፤ ያን​ዱን ስሙን ብሔ​ሞት አል​ኸው፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ስሙን ሌዋ​ታን አል​ኸው።

50 በየ​ራ​ሳ​ቸ​ውም ለየ​ሃ​ቸው፤ የና​ጌብ ውኃ ያለ​በት ያ ሰባ​ተ​ኛው እጅ ሊወ​ስ​ና​ቸው አይ​ች​ል​ምና፥

51 አራቱ ተራ​ሮች ባሉ​በት በዚያ እርሱ በው​ስጡ ይኖር ዘንድ ለብ​ሔ​ሞት ከስ​ድ​ስቱ እጅ አን​ዱን እጅ የብ​ስን ሰጠ​ኸው።

52 “ለሌ​ዋ​ታ​ንም የባ​ሕ​ሩን ሰባ​ተኛ እጅ ሰጠ​ኸው፤ ለም​ት​ወ​ዳ​ቸው ምግብ ይሆኑ ዘን​ድም ጠበ​ቅ​ሃ​ቸው።

53 በስ​ድ​ስ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም ቀን በፊ​ትህ እን​ስ​ሳን፥ የሰ​ማይ ወፎ​ች​ንና የዱር አው​ሬ​ዎ​ችን ታስ​ገኝ ዘንድ ምድ​ርን አዘ​ዝ​ሃት።

54 በዚ​ህም ሁሉ ላይ አዳ​ምን ገዥ አድ​ር​ገህ ሾም​ኸው፤ አስ​ቀ​ድ​መህ በፈ​ጠ​ር​ኸው ፍጥ​ረት ላይም ገዥ ሆነ። በእ​ር​ሱም ምክ​ን​ያት የመ​ረ​ጥ​ኸን እኛ ወገ​ኖ​ችህ ከእ​ርሱ ተገ​ኘን።

55 “አቤቱ፥ ይህን ሁሉ በፊ​ትህ ተና​ገ​ርሁ፤ ይህን ዓለም ሰለ እና​ንተ ፈጠ​ር​ሁት ብለ​ሃ​ልና።

56 ከአ​ዳም የተ​ወ​ለዱ ሌሎች አሕ​ዛብ ግን እንደ ኢም​ንት ናቸው፤ እንደ ምራ​ቅም ይመ​ስ​ላሉ፤ እንደ አፍ​ሻት ጠብ​ታም ናቸው፤ ደስ​ታ​ቸ​ውም እንደ ኢም​ንት ነው።

57 አሁ​ንም እነሆ እንደ ኢም​ንት ናቸው ያል​ሃ​ቸው እነ​ዚያ አሕ​ዛብ እነሆ በእኛ ላይ ሠለ​ጠኑ፤ ረገ​ጡ​ንም።

58 የም​ወ​ደው የበ​ኸር አን​ድያ ልጄ ያል​ኸን እኛ ወገ​ኖ​ችህ ግን በአ​ሕ​ዛብ እጅ ገባን።

59 ነገር ግን ዓለ​ምን ስለ እኛ ከፈ​ጠ​ር​ኸው ዓለ​ማ​ች​ንን ለምን አን​ወ​ር​ስም? ይህስ እስከ መቼ ድረስ ነው?”