Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa

መጽ​ሐፈ ዕዝራ ሱቱ​ኤል 5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ህም በኋላ ይህን ነገር ተና​ግሬ በጨ​ረ​ስሁ ጊዜ ባለ​ፈ​ችው በዚ​ያች ሌሊት አስ​ቀ​ድሞ ወደ እኔ የመ​ጣው ያ መል​አክ ወደ እኔ ተላከ።

2 እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ዕዝራ ሆይ፥ ተነሥ፤ እነ​ግ​ርህ ዘንድ ወደ አንተ የመ​ጣሁ የእ​ኔን ቃል ስማ።”

3 እኔም አል​ሁት፥ “ጌታዬ ተና​ገር፤” እር​ሱም አለኝ፥ “በአ​ንድ ሰፊ ቦታ ባሕር አለች፤ እር​ስ​ዋም ሰፊና ጥልቅ ናት።

4 ጠባብ የመ​ግ​ቢያ መን​ገ​ድም አላት፤ የመ​ስኖ ውኃ ቦይ ያህ​ልም ትሆ​ና​ለች።

5 ያያ​ትና ያገ​ኛት ዘንድ ወደ​ዚ​ያች ባሕር ሊገባ የወ​ደደ ቢኖር ያን ጠባ​ቡን መግ​ቢ​ያ​ዋን ካላ​ለፈ ወደ አደ​ባ​ባ​ይዋ መግ​ባት እን​ዴት ይች​ላል?

6 ወይም በሜዳ የተ​ሠ​ራች፥ ከበ​ረ​ከ​ቱም ሁሉ የተ​መ​ላች አን​ዲት ከተማ አለች።

7 የመ​ግ​ቢ​ያ​ዋም መን​ገድ ጠባብ ነው፤ በገ​ደል ውስ​ጥም ናት፤ በቀ​ኝዋ እሳት፥ በግ​ራ​ዋም ጥልቅ ውኃ አለ።

8 አን​ዲት መን​ገድ በው​ኃና በእ​ሳት መካ​ከል አለች፤ መን​ገ​ድ​ዋም ከአ​ንድ ሰው እግር ጫማ በቀር አት​ች​ልም።

9 ይህች ከተማ የተ​ሰ​ጠ​ችው የሚ​ወ​ር​ሳት ሰው ቢኖር ያን ጠባ​ቡን መን​ገድ ካላ​ለፈ ርስ​ቱን እን​ዴት ያገ​ኛል?”

10 እኔም፥ “አቤቱ፥ እን​ደ​ዚሁ ነው” አል​ሁት። እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ምድ​ራ​ቸው፥ ዕድል ፈን​ታ​ቸ​ውም እን​ዲሁ ነው።

11 ዓለ​ምን ስለ እነ​ርሱ ፈጥ​ሬ​ዋ​ለ​ሁና።

12 አዳ​ምም ትእ​ዛ​ዜን ባፈ​ረሰ ጊዜ የዚህ ዓለም ጎዳ​ናው ሰን​ከ​ል​ካ​ላና ጠባብ፥ ጐድ​ጓ​ዳና የከፋ፥ መከ​ራው የበዛ፥ ጻዕ​ርና ጋርን የተ​መላ ሆነ።

13 የዚ​ያ​ኛው ዓለም ግን ጎዳ​ናው ታላቅ ነው፤ ሰፊም ነው፤ ብሩ​ህም ነው፤ ሞት የሌ​ለ​በት የሕ​ይ​ወት ፍሬ​ንም ያፈ​ራል።

14 ሕያ​ዋን የም​ት​ሆኑ እና​ን​ተም ያን ሰን​ከ​ል​ካ​ላና ያን ኀጢ​አት ካላ​ለ​ፋ​ች​ሁት ለእ​ና​ንተ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ውን ማግ​ኘት አት​ች​ሉም።

15 አሁ​ንስ አፈር የም​ት​ሆን አንተ ለምን ትታ​ወ​ካ​ለህ? ሟች የም​ት​ሆን አን​ተስ ለምን ትና​ወ​ጣ​ለህ?

16 ያለ​ውን ነው እንጂ የሚ​መ​ጣ​ውን በል​ብህ ለምን አታ​ስ​ብም?”


የኃ​ጥ​ኣን ዕድል ፈንታ

17 እኔም መልሼ አል​ሁት፥ “አቤቱ ጌታዬ፥ ጻድ​ቃን ይህን ዓለም እን​ደ​ሚ​ወ​ር​ሱት፥ ኃጥ​ኣን ግን እን​ደ​ሚ​ጠፉ አንተ በሕ​ግህ እነሆ፥ ተና​ገ​ርህ።

18 ጻድ​ቃን ሰፊ​ውን ተስፋ እያ​ደ​ረጉ ጠባ​ቡን ይታ​ገ​ሡ​ታ​ልና፤ ጠባ​ቡን የሚ​ታ​መኑ ኃጥ​ኣን ግን ሰፊ​ውን አያ​ገ​ኙ​ትም።”

19 እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “አንተ በፍ​ርድ ከአ​ንዱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ት​ሻል አይ​ደ​ለ​ህም፤ ከል​ዑ​ልም አንተ የም​ት​ራ​ቀቅ አይ​ደ​ለ​ህም።

20 የሠ​ራ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕጉን ያቃ​ለሉ እነ​ዚያ ይጥፉ፤

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕጉን ሠር​ተው በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ኖሩ አዟ​ቸ​ዋ​ልና። ሕጉን ቢጠ​ብቁ ግን ባል​ተ​ፈ​ረ​ደ​ባ​ቸ​ውም ነበር።

22 ኃጥ​ኣን ግን ካዱት፤ ተዉ​ትም፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም ክፉ አሳ​ብን አሰቡ።

23 ሽን​ገ​ላ​ንና ዐመ​ፅን ለራ​ሳ​ቸው ገን​ዘብ አደ​ረጉ፤ ከዚ​ህም ሁሉ ጋር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለም አሉ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ተዉ።

24 ሕጉ​ንም ካዱ፤ ቃል ኪዳ​ኑ​ንም ቸል አሉ፤ በሥ​ር​ዐ​ቱም አል​ታ​መ​ኑም፤ ሥራ​ው​ንም ናቁ፤ አም​ል​ኮ​ቱ​ንም አላ​ሰ​ቡም።

25 ስለ​ዚህ የተ​ራ​ቈ​ተው ለተ​ራ​ቈ​ቱት ነው፤ የተ​ሞ​ላ​ውም ለተ​ሞ​ሉት ነው።


የመ​ሲሕ መን​ግ​ሥት

26 “እኔ የነ​ገ​ር​ሁህ ምል​ክት የሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ወራት እነሆ፥ ይመ​ጣ​ልና፥ ዛሬ የም​ት​ታይ ከተማ ታል​ፋ​ለች፤ ዛሬ የተ​ሰ​ወ​ረች ምድ​ርም ትገ​ለ​ጻ​ለች።

27 እኔ ከነ​ገ​ር​ሁህ ከክፉ ሥራ የዳነ ሁሉ ክብ​ሬን የሚ​ያይ እርሱ ነው።

28 የእኔ መሲሕ አብ​ረ​ውት ካሉት ጋር ይገ​ለ​ጣ​ልና፥ የሚ​ነ​ሡ​ት​ንም ደስ ያሰ​ኛ​ቸ​ዋል።

29 ከዚህ በኋላ ልጄ መሲሑ ይፈ​ጽ​ማል፤ አእ​ምሮ ያለ​ውም ሰው ሁሉ ይፈ​ጽ​ማል፤

30 ዓለ​ምም እንደ ቀድ​ሞው ሰባት ቀን ዝም ያለ​ውን ያህል ወደ ቀድሞ አነ​ዋ​ወሩ ይመ​ለ​ሳል፤ የሚ​ቀ​ርም የለም።

31 ከሰ​ባት ቀን በኋ​ላም የነ​ቃ​በት ጊዜ የሌለ ሰው ይነ​ሣል፤ የመ​ዋቲ ሰው ዓለ​ምም ያል​ፋል።

32 ምድ​ርም የተ​ቀ​በ​ሩ​ባ​ትን ሰዎች ትመ​ል​ሳ​ለች፤ መሬ​ትም በው​ስጡ ያረ​ፉ​ትን ሰዎች ይመ​ል​ሳል፤ ከዚ​ህም በኋላ አብ​ያተ ነፍስ በው​ስ​ጣ​ቸው የተ​ቀ​መጡ ነፍ​ሳ​ትን ይመ​ል​ሳሉ።

33 ያን​ጊ​ዜም ልዑል በፈ​ጠ​ረው በዙ​ፋኑ ላይ ይገ​ለ​ጣል፤ ቸር​ነ​ቱም ትመ​ጣ​ለች፤ ይቅ​ር​ታ​ውም ትመ​ለ​ሳ​ለች፤ ትዕ​ግ​ሥ​ቱም ትሰ​በ​ሰ​ባ​ለች።

34 ቍርጥ ፍርድ ብቻ ይቀ​ራል፤ ጽድቅ ትጸ​ና​ለች፤ ሃይ​ማ​ኖ​ትም ትገ​ለ​ጣ​ለች።

35 ሰውን ሥራው ይከ​ተ​ለ​ዋል፤ ዋጋ​ውም ይገ​ለ​ጣል፤ ቅን​ነ​ቱም ትነ​ቃ​ለች፤ ኀጢ​አ​ቱም አታ​ን​ቀ​ላ​ፋም።

36 የቍ​ርጥ ፍርድ ጕድ​ጓድ በዕ​ረ​ፍት ቦታ አን​ጻር ይከ​ፈ​ታል። በደ​ስታ ገነ​ትም አን​ጻር እሳተ ገሃ​ነም ይገ​ለ​ጣል።

37 “ያን​ጊ​ዜም ልዑል ከሙ​ታን የተ​ነሡ አሕ​ዛ​ብን፦ ‘እነሆ እዩ፤ የካ​ዳ​ች​ሁ​ትም ማን እንደ ሆነ ዕወቁ፤ ያል​ተ​ገ​ዛ​ችሁ ለማን ነው? የና​ቃ​ች​ሁ​ትስ የማ​ንን ትእ​ዛዝ ነው?” ይላ​ቸ​ዋል።

38 እነሆ፥ ወደ ፊታ​ችሁ እዩ፤ በወ​ዲህ ደስ​ታና ዕረ​ፍት አለ፤ በወ​ዲ​ያም ፍር​ድና እሳት አለ።’

39 “ልዑል በፍ​ርድ ቀን አሕ​ዛ​ብን እን​ዲህ ይላ​ቸ​ዋል፦ ‘የፍ​ርድ ቀንስ እን​ዲህ ናት፤ ፀሐይ፥ ጨረ​ቃም፥ ከዋ​ክ​ብ​ትም የሉ​አ​ትም።

40 ደመ​ናም፥ መብ​ረ​ቅም፥ ነጐ​ድ​ጓ​ድም፥ ነፋ​ስም፥ ውኃም፥ ሰማ​ይም፥ ጨለ​ማም፥ ሌሊ​ትም፥ መዓ​ል​ትም የሉ​አ​ትም፤

41 ክረ​ምት፥ በጋም፥ መከ​ርም፥ ብር​ድም፥ ሐሩ​ርም፥ ጥቅል ነፋስ፥ በረድ፥ ውርጭ፥ ጉም፥ ዝናም፥ ጠል የለ​ባ​ትም።

42 ማታና ጧት፥ ብር​ሃ​ንና ብል​ጭ​ል​ጭታ፥ ፋናና መብ​ራት፥ ሁሉ ለእ​ርሱ የተ​ጠ​በ​ቀ​ለ​ትን ያይ​በት ዘንድ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጌ​ት​ነቱ ብር​ሃን ብቻ በቀር ይህ ሁሉ የለም።

43 የዚ​ያች ሰዓት ርዝ​መቷ እንደ ሰባት ዓመት ይሆ​ናል።

44 ፍር​ዱም፥ ቅጣ​ቱም ይህ ነው’ ይህ​ንም ለአ​ንተ ብቻ ነገ​ርሁ።”


የሚ​ድኑ ጥቂ​ቶች ስለ​መ​ሆ​ና​ቸው

45 እኔም እን​ዲህ አል​ሁት፥ “አሁ​ንም አቤቱ፥ ትእ​ዛ​ዝ​ህን ጠብ​ቀው የኖሩ ብፁ​ዓን ናቸው።

46 ነገር ግን ስለ ጠየ​ቅ​ሁህ ነገር ከሕ​ያ​ዋን መካ​ከል የማ​ይ​በ​ድል ማን​ነው? ከተ​ወ​ለ​ደስ ወገን ሕግ​ህን ያል​ተወ ማን​ነው?

47 አሁ​ንም በሚ​መ​ጣው ዓለም ደስ ታሰ​ኛ​ቸው ዘንድ ያለህ ጻድ​ቃን ጥቂት እንደ ሆኑ፥ የሚ​ፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ውም ብዙ​ዎች እንደ ሆኑ አያ​ለሁ።

48 ከዚ​ህም ያሳ​ተን፥ ወደ ጥፋ​ትም የመ​ራን፥ ወደ ሞት ጎዳ​ናና ወደ ጥፋት መን​ገ​ድም የወ​ሰ​ደን፥ ከዛሬ ጀምሮ ከእኛ ሕይ​ወ​ትን ያራ​ቃት፥ ክፉ ልቡና በእኛ ጸን​ት​ዋ​ልና። ይህም በተ​ወ​ለዱ ሁሉ ላይ ነው እንጂ በጥ​ቂ​ቶች ብቻ አይ​ደ​ለም።”

49 መል​አ​ኩም መለ​ሰ​ልኝ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ስማኝ ልን​ገ​ርህ፤ ዳግ​መ​ኛም አስ​ተ​ም​ር​ሃ​ለሁ።

50 ስለ​ዚህ ነገር ልዑል ሁለት ዓለ​ምን እንጂ አንድ ዓለ​ምን ብቻ አል​ፈ​ጠ​ረም።

51 አንተ ግን የጻ​ድ​ቃን ቍጥ​ራ​ቸው ጥቂት ነው፤ ብዙ​ዎ​ችም አይ​ደ​ሉም፤ የኃ​ጥ​ኣን ግን ቍጥ​ራ​ቸው ብዙ ነው ብለ​ሃ​ልና፥

52 እር​ሳ​ሱን ከሸ​ክላ ጋር ሥራ።”

53 እኔም አል​ሁት፥ “አቤቱ፥ ይህ እን​ዴት ይቻ​ለ​ኛል።”

54 እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ይህን ብቻ አይ​ደ​ለም፥ ነገር ግን ምድ​ርን ጠይ​ቃት፤ ትነ​ግ​ር​ሃ​ለ​ችም፤ ተና​ገ​ራት፤ ትመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለ​ችም።

55 እነሆ፥ ወር​ቁን፥ ብሩ​ንም፥ ናሱ​ንም፥ ብረ​ቱ​ንና እር​ሳ​ሱን፥ ሸክ​ላ​ው​ንም አንቺ ታስ​ገ​ኚ​ዋ​ለሽ በላት።

56 ብር ከወ​ርቅ፥ ናስም ከብር፥ ብረ​ትም ከናስ፥ እር​ሳ​ስም ከብ​ረት፥ ሸክ​ላም ከእ​ር​ሳስ ይበ​ዛል።

57 እን​ግ​ዲህ አንተ ራስህ ዕወቅ፥ የት​ኛው ይከ​ብ​ራል? የት​ኛ​ውስ ይወ​ደ​ዳል? የሚ​በ​ዛው ነውን? ወይስ የሚ​ያ​ን​ሰው ነው?”

58 እኔም መለ​ስ​ሁ​ለት እን​ዲ​ህም አል​ሁት፥ “ጌታዬ ሆይ የሚ​ያ​ን​ሰው ይወ​ደ​ዳል፤ የሚ​በ​ዛ​ውም ይረ​ክ​ሳል።”

59 እር​ሱም መለ​ሰ​ልኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “ያሰ​ብ​ኸ​ውን አንተ ራስህ መዝ​ነው፤ ከብ​ዙው ካለው ይልቅ፥ ከጥ​ቂቱ ያለው እጅግ ደስ ይለ​ዋ​ልና ከእኔ ዘንድ የሚ​ገኝ የጻ​ድ​ቃን ደስ​ታ​ቸው እን​ደ​ዚሁ ነው።

60 ስለ​ሚ​ድኑ ስለ ጥቂ​ቶች ደስ ይለ​ኛል፤ ክብ​ሬን ያገ​ኛ​ሉና። ስሜም በእ​ነ​ርሱ ተመ​ስ​ግ​ኖ​አ​ልና።

61 ስለ​ሚ​ጠፉ ስለ ብዙ​ዎች ልቡ​ና​ዬን አላ​ሳ​ዝ​ነ​ውም። እነ​ርሱ ዛሬ በእ​ሳት ተመ​ስ​ለ​ዋ​ልና፥ እንደ እሳት ነበ​ል​ባ​ልም ሆነ​ዋ​ልና፥ እንደ ጢስም ነድ​ደ​ውና ተን​ነው ጠፍ​ተ​ዋ​ልና።”


የዕ​ዝራ ልቅሶ

62 እኔም መለ​ስ​ሁ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አል​ሁት፥ “ምድር ሆይ እን​ዳ​ንቺ ያለ ልዩ ፍጥ​ረት ከመ​ሬ​ትሽ ለምን ተገኘ?

63 ነገር ግን ክፉ ልቡና ከሚ​ፈ​ጠ​ር​ልን ይልቅ ባይ​ፈ​ጠ​ር​ልን በተ​ሻ​ለን ነበር።

64 ክፉ ልብም ከእኛ ጋር ያድ​ጋል፤ ስለ እር​ሱም ይፈ​ረ​ድ​ብ​ናል፤ ሳና​ው​ቀው እን​ጐ​ዳ​ለ​ንና።

65 የሰው ልጆች ያል​ቅሱ፤ የም​ድረ በዳ አው​ሬ​ዎች ግን ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ ከአ​ዳም የተ​ወ​ለዱ ሁሉም ያል​ቅሱ፤ የእ​ን​ስሳ መን​ጋ​ዎ​ችም ደስ ይበ​ላ​ቸው።

66 የሚ​ጠ​ብ​ቃ​ቸው ቍርጥ ፍርድ ስለ​ሌለ፥ ፍር​ድ​ንም ገሃ​ነ​ም​ንም ስለ​ማ​ያ​ው​ቁት፥ ከሞ​ቱም በኋላ መነ​ሣ​ትን ተስፋ ስለ​ማ​ያ​ደ​ርጉ እነ​ርሱ ከእኛ እጅግ ይሻ​ላ​ሉና።

67 የም​ን​ነ​ሣው ትን​ሣኤ ምን ይጠ​ቅ​መ​ናል?

68 የተ​ወ​ለ​ድን ሁሉ በኀ​ጢ​አት ተሰ​ጠ​ምን፤ ዐመ​ፅ​ንም ተሞ​ላን፤ በደ​ላ​ች​ንም ጸና።

69 ከሞ​ትን በኋላ ወደ ፍርድ ባን​ሄድ በተ​ሻ​ለን ነበር አል​ሁት።”

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos