ሶፎንያስ 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ አላግጠዋልና፥ እየታበዩም ተናግረዋልና ይህ ስለ ትዕቢታቸው ያገኛቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከትዕቢታቸው የተነሣ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ሰድበው ዘብተውበታልና፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከትዕቢታቸው የተነሣ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤ በሠራዊት ጌታ ሕዝብ ላይ አላግጠዋልና፥ በኩራትም ተናግረዋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞአብና የዐሞን ሕዝብ በሠራዊት አምላክ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ስላፌዙና ስለ ዛቱ ይህ ቅጣት የሚደርስባቸው ለትዕቢታቸው አጸፋ የሚከፈል ዕድል ፈንታቸው ስለ ሆነ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ አላግጠዋልና፥ እየታበዩም ተናግረዋልና ይህ ስለ ትዕቢታቸው ያገኛቸዋል። |
ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ አሉትም፥ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ማፈርን እስከ መቼ እንቢ ትላለህ? ያመልኩኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ።
የሞዓብን ትዕቢትና እጅግ መኵራቱን ሰምተናል፤ ትዕቢቱንም አስወገድሁ፤ ጥንቈላህ እንዲህ አይደለምና፥ እንዲህም አይደለም፤
እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጎረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፥ “እነሆ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።
ጤት። ግዳጅዋ ከእግርዋ በታች ነበረ፤ ፍጻሜዋን አላሰበችም፤ ከባድ ሸክምን ተሸከመች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ አቤቱ! ጠላት ከፍ ከፍ ብሎአልና መከራዬን ተመልከት።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በእጆችህ አጨብጭበሃልና፥ በእግሮችህም አሸብሽበሃልና፥ ሰውነትህም በእስራኤል ምድር ላይ ደስ ብሎአታልና፤
በፊቱ አንጻር በቆምህ ቀን፥ አሕዛብ ጭፍራውን በማረኩበት፥ እንግዶችም በበሩ በገቡበት፥ በኢየሩሳሌምም ዕጣ በተጣጣሉበት ቀን አንተ ደግሞ ከእነርሱ እንደ አንዱ ነበርህ።
በተሰነጠቀም ዓለት ውስጥ እንደሚኖር- ማደሪያውንም ከፍ ከፍ እንደሚያደርግ፥ በልቡም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? እንደሚል፥ የልብህ ትዕቢት እጅግ አኵርቶሃል።
እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።