እግዚአብሔርም፥ “የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳና አራዊት፥ እስከ ተንቀሳቃሽም፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና” አለ።
ሶፎንያስ 1:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፣ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን፣ ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም።” መላዪቱ ምድር፣ በቅናቱ ትበላለች፤ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ፣ ድንገተኛ ፍጻሜ ያመጣባቸዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ አስፈሪ ፍፃሜ ያመጣባቸዋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት በዚያን ቀን ሰዎችን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እንደ እሳት ባለው ቅናቱ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ ይህም የሚሆነው በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በድንገት የሚያልቁ ስለ ሆነ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፥ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች። |
እግዚአብሔርም፥ “የፈጠርሁትን ሰው ከምድር ላይ አጠፋለሁ፤ ከሰው እስከ እንስሳና አራዊት፥ እስከ ተንቀሳቃሽም፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ፤ ስለ ፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና” አለ።
ሮብዓምም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሠራ፤ አባቶቹ በሠሩት ኀጢአትና በደል ሁሉ እንደ አስቀኑት በሠራው ኀጢአት አስቀናው።
በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች። ጻድቅ በሞተ ጊዜ ጸጸትን ይተዋል፥ የኀጢአተኛ ሞት ግን በእጅ የተያዘና ሣቅ ይሆናል።
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ለእስራኤል ኀያላን ወዮላቸው! በጠላቶች ላይ ቍጣዬ አይበርድም፤ ጠላቶችንም እበቀላለሁ።
እንግዲህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።”
ምድሪቱም ባድማ ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም አደባባይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ አጠፋለሁ።
ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው እንዳይቀመጥባቸው አጠፋቸዋለሁ።
ቅንአቴንም በአንቺ ላይ አደርጋለሁ፤ በመዓትም ያደርጉብሻል፤ አፍንጫሽንና ጆሮሽንም ከአንቺ ይቈርጣሉ፤ ከአንቺም የቀረ በሰይፍ ይወድቃል፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽንም ማርከው ይወስዳሉ፤ ከአንቺም የቀሩትን እሳት ትበላቸዋለች።
ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ፤ ወርቃቸውም ይረክሳል፤ በእግዚአብሔር መዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው አያድናቸውም። እርሱ የኀጢአታቸው እንቅፋት ሆኖአልና ሰውነታቸውን አያጠግቡም፤ ሆዳቸውንም አይሞሉም።
መዓቴንና የቍጣዬን ትኵሳት ሁሉ አፈስስባቸው ዘንድ ፍርዴ አሕዛብን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነውና፥ ምድርም ሁሉ በቅንዓቴ እሳት ትበላለችና ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።
በዚያም ቀን ቍጣዬ ይነድድባቸዋል፤ እተዋቸውማለሁ፤ ፊቴንም ከእነርሱ እመልሳለሁ፤ ለጠላቶቻቸውም መብል ይሆናሉ፤ በዚያም ቀን፦ በእውነት አምላካችን እግዚአብሔር ትቶናልና፥ በእኛም መካከል የለምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገኘን እስኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገርና ጭንቀት ይደርስባቸዋል።