ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ሰፈረባት፤ በዙሪያዋም ዕርድ ሠራባት።
ዘካርያስ 8:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፣ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የአራተኛው፣ የአምስተኛው፣ የሰባተኛውና የዐሥረኛው ወር ጾሞች ለይሁዳ ቤት የደስታ፣ የተድላና የሐሤት በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህ እውነትንና ሰላምን ውደዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም፥ የአምስተኛው፥ የሰባተኛው፥ የአሥረኛው ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ፥ የሐሤትም በዓላት ይሆናሉ፤ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በአራተኛው፥ በአምስተኛው፥ በሰባተኛውና በዐሥረኛው ወር ትጠብቁት የነበረው ጾም ሁሉ ለይሁዳ ሕዝብ የተድላና የደስታ በዓል ይሆንላቸዋል፤ እናንተ ግን እውነትንና ሰላምን ውደዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፥ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ። |
ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ሰፈረባት፤ በዙሪያዋም ዕርድ ሠራባት።
በሰባተኛው ወር ግን የመንግሥት ዘር የነበረ የኤልሴማ ልጅ የናታንዩ ልጅ እስማኤል መጣ፤ ከእርሱም ጋር ዐሥር ሰዎች ነበሩ፤ ጎዶልያንም መታው፤ ሞተም፤ ከእርሱም ጋር በመሴፋ የነበሩትን አይሁድንና ከለዳውያንንም ገደላቸው።
በዚያም ቀን እንዲህ ትላለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈጥተኸኛልና፥ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፥ ዳግመኛም ይቅር ብለኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
በእግዚአብሔር የተሰበሰቡም ይመለሳሉ፤ በደስታም ተመልሰው ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘለዓለም ደስታም በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታንም ያገኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘንና ትካዜም ይጠፋሉ።
እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ ወደ ጽዮንም በደስታና በሐሤት ይመጣሉ፤ የዘለዓለምም ክብር በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፤ ኀዘንና ልቅሶም ይወገዳሉ።
አንተ ግን ገብተህ ከአፌ የጻፍኸውን የእግዚአብሔርን ቃል በጾም ቀን በእግዚአብሔር ቤት በሕዝቡ ጆሮ በክርታሱ አንብብ፤ ደግሞም ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው።
በሴዴቅያስም በዐሥራ አንደኛው ዓመተ መንግሥት በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በዘጠነኛው ቀን ከተማዪቱ ተለያየች።
ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር ከወሩም በዐሥረኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ መጥተው ከበቡአት፤ በዙሪያዋም አራት ክንድ ግንብ ሠራ።
በአራጣ ባያበድር፥ አትርፎም ባይወስድ፥ እጁንም ከኀጢአት ቢመልስ፥ በሰውና በሰው መካከልም የእውነትን ፍርድ ቢፈርድ፥
ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ ባለፉት ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መለየትና ማልቀስ ይገባኛልን? ብለው ይናገሩ ዘንድ ልኮአቸው ነበር።
ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?
የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፣ በበር አደባባያችሁም የእውነትንና የሰላምን ፍርድ ፍረዱ፣
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፥ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፣ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች፣ የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ተራራ የተቀደሰ ተራራ ይባላል።