Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 24:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዘጠነኛው ዓመት፣ በዐሥረኛው ወር፣ በዐሥረኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዘጠነኛው ዓመት፥ በአሥረኛው ወር፥ ከወሩም በአሥረኛው ቀን፥ የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በተሰደድን በዘጠነኛው ዓመት፥ በዐሥረኛው ወር፥ በዐሥረኛው ቀን፥ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረኝ፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በዘጠነኛው ዓመት በአሥረኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 24:1
17 Referencias Cruzadas  

የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ዮአ​ኪን ከእ​ናቱ፥ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቹም፥ ከአ​ለ​ቆ​ቹም፥ ከጃ​ን​ደ​ረ​ቦ​ቹም ጋር ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በነ​ገሠ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ዓመት ያዘው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጥ​ተው ከበ​ቡ​አት።


ሴዴ​ቅ​ያ​ስም በነ​ገሠ በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርና ሠራ​ዊቱ ሁሉ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ መጥ​ተው ከበ​ቡ​አት፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም አራት ክንድ ግንብ ሠራ።


ንጉሡ ዮአ​ኪን በተ​ማ​ረከ በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት፥ ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን፥


እን​ዲ​ህም ሆነ፥ በሰ​ባ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይጠ​ይቁ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሰዎች መጡ፤ በፊ​ቴም ተቀ​መጡ።


እን​ግ​ዲህ በደ​ላ​ችሁ በላ​ያ​ችሁ ላይ ይመ​ለ​ሳል፤ እና​ን​ተም የጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ኀጢ​አት ትሸ​ከ​ማ​ላ​ችሁ፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”


“የሰው ልጅ ሆይ! የዚ​ህን ቀን፥ የዛ​ሬን ቀን ስም ጻፍ፤ በዚህ ቀን የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይመ​ጣ​ልና።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ከወሩ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


በዐ​ሥ​ረ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሃያ ሰባ​ተ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት በሦ​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በተ​ማ​ረ​ክን በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት በዐ​ሥ​ረ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያመ​ለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፦ ከተ​ማ​ዪቱ ተያ​ዘች አለኝ።


በተ​ማ​ረ​ክን በሃያ አም​ስ​ተ​ኛው ዓመት በዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ ከወሩ በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን፥ ከተ​ማ​ዪቱ ከተ​መ​ታች በኋላ በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ዓመት፥ በዚ​ያው ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረ፤ እር​ሱም ወደ​ዚያ ወሰ​ደኝ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ቀን በቤቴ ተቀ​ምጬ ሳለሁ፥ የይ​ሁ​ዳም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች በፊቴ ተቀ​ም​ጠው ሳሉ፥ በዚያ የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በላዬ መጣ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፣ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos