ሩት 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንደ ገና አለቀሱ፣ ዖርፋም አማትዋን ሳመች፣ ሩት ግን ተጠጋቻት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንደ ገና አለቀሱ፤ ከዚያም ዖርፋ ዐማቷን ስማ ተሰናበተቻት፤ ሩት ግን ልትለያት ስላልፈለገች ተጠመጠመችባት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንደገና አለቀሱ፥ ዖርፋም አማቷን ሳመች፥ ሩት ግን አማቷ ጋር ተጣበቀች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንደገና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ በዚህ ጊዜ ዖርፋ ዐማትዋን ስማ ተሰናበተች፤ ሩት ግን ከዐማትዋ ላለመለየት ወሰነች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንደ ገና አለቀሱ፤ ዖርፋም አማትዋን ሳመች፤ ሩት ግን ተጠጋቻት። |
ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ ንጉሡም ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ንጉሡም ቤርዜሊን አቅፎ ሳመው፤ መረቀውም፤ ወደ ስፍራውም ተመለሰ።
ኤልሳዕም በሬዎቹን ተወ፤ ኤልያስንም ተከትሎ ሄደ፥ “አባቴንና እናቴን እስማቸው ዘንድ፥ እባክህ ተወኝ፤ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። እርሱም“ሂድና ተመለስ፤ ምን አድርጌልሃለሁ?” አለው።
እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፤ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፤ በሀገራቸውም ያርፋሉ፤ መጻተኞችም ከእነርሱ ጋር አንድ ይሆናሉ፤ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጨመራሉ።
የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።
ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።
አምነው የተከተሉት ሰዎችም ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ከአርዮስፋጎስ ባለሥልጣኖች ወገን የሚሆን ዲዮናስዮስ ነበር፤ ደማሪስ የምትባል ሴትም ነበረች፤ ሌሎችም አብረዋቸው ነበሩ።
እነርሱ እስኪያድጉ ድረስ ትቆያላችሁን? ስለ እነርሱስ ባል ማግባት ትተዋላችሁን? ልጆቼ ሆይ፥ እንዲህ አይደለም፣ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ወጥቶአልና ከእናንተ የተነሣ እጅግ ተመርሬአለሁ።
ቦዔዝም፦ ባልሽ ከሞተ በኋላ አባትሽንና እናትሽን የተወለድሽባትንም ምድር ትተሽ ቀድሞ ወደማታውቂው ሕዝብ እንደ መጣሽ፥ ለአማትሽ ያደረግሽውን ነገር ሁሉ ፈጽሞ ሰምቻለሁ።