ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ መጡ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደለ።
ሮሜ 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ግብር ታገቡላቸዋላችሁ፤ ለዚህ ሥራ የተሾሙ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግብር የምትከፍሉትም ደግሞ ለዚህ ነው፤ ባለሥልጣናቱ፣ በዚሁ ተግባር ላይ የተሰማሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ምክንያት ደግሞ ግብር ትከፍላላችሁና፤ በዚህ ነገር የሚተጉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግብር የምትከፍሉትም ስለዚህ ነው፤ ባለሥልጣኖች በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩት እግዚአብሔርን ለማገልገል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ደግሞ ትገብራላችሁና፤ በዚህ ነገር የሚተጉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና። |
ከደማስቆም ሶርያውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ሊረዱ መጡ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎችን ገደለ።
አሁንም ይህች ከተማ የተሠራች እንደ ሆነ፥ ቅጥርዋም የታደሰ እንደ ሆነ፥ ግብርና ቀረጥ መጥንም እንደማይሰጡ፥ ንጉሡ ይወቅ፤ ይህም መንግሥትን ይጐዳል።
በኢየሩሳሌምም እጅግ ኀያላን ነገሥታት ነበሩ፤ በወንዝም ማዶ ያለውን ሀገር ሁሉ ይገዙ ነበር፤ ግብርንና እጅ መንሻንም ይቀበሉ ነበር።
ይህን የእግዚአብሔርን ቤት ይሠሩ ዘንድ ለአይሁድ ሽማግሌዎች የምታደርጉትን፥ በወንዝ ማዶ ካለው ሀገር ከሚመጣው ግብር ከንጉሡ ገንዘብ ለእነዚህ ሰዎች ወጭውን በትጋት እንድትሰጡአቸው፥ ሥራም እንዳታስፈቱአቸው አዝዣለሁ።
እንዲህም እያሉ ይከስሱት ጀመር፥ “ይህ ሰው ለቄሣር ግብር እንዳይሰጡ ሲከለክልና ሕዝቡን ሲያሳምፅ፥ ራሱንም የእስራኤል ንጉሥ ክርስቶስን ሲያደርግ አገኘነው።”
የሚመክርም በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥም በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛም በትጋት ይግዛ፤ የሚመጸውትም በደስታ ይመጽውት።
ለሁሉም እንደሚገባው አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን ስጡ፤ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ስጡ፤ ዐሥራት ለሚገባው ዐሥራትን ስጡ፤ ሊፈሩት የሚገባውን ፍሩ፤ ክብር የሚገባውንም አክብሩ።