Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 13:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ግብር የምትከፍሉትም ደግሞ ለዚህ ነው፤ ባለሥልጣናቱ፣ በዚሁ ተግባር ላይ የተሰማሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በዚህም ምክንያት ደግሞ ግብር ትከፍላላችሁና፤ በዚህ ነገር የሚተጉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ግብር የምትከፍሉትም ስለዚህ ነው፤ ባለሥልጣኖች በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩት እግዚአብሔርን ለማገልገል ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ስለ​ዚ​ህም ግብር ታገ​ቡ​ላ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ለዚህ ሥራ የተ​ሾሙ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸ​ውና፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ስለዚህ ደግሞ ትገብራላችሁና፤ በዚህ ነገር የሚተጉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 13:6
18 Referencias Cruzadas  

ሶርያውያንም የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ለመርዳት ከደማስቆ በመጡ ጊዜ ዳዊት ሃያ ሁለት ሺሕ ሰው ገደለ።


ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ለሕዝቡም ሁሉ ፍትሕንና ጽድቅን አሰፈነላቸው።


ከዚህም በላይ ይህች ከተማ ከተሠራች፣ ቅጥሮቿም እንደ ገና ከተገነቡ፣ ቀረጥና እጅ መንሻ ወይም ግብር እንደማይከፍሉ፣ የቤተ መንግሥቱም ገቢ እንደሚቀንስ በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን።


ኢየሩሳሌም ከኤፍራጥስ ማዶ ያለውን አገር ሁሉ የገዙ፣ ቀረጥ፣ ግብርና እጅ መንሻም ይቀበሉ የነበሩ ኀያላን ነገሥታት ነበሯት።


በተጨማሪም የአይሁድ መሪዎች ይህን የእግዚአብሔር ቤት እንደ ገና ሲሠሩ፣ እናንተ ምን እንደምታደርጉላቸው ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤ ሥራውም እንዳይቋረጥ የእነዚህ ሰዎች ወጪ በሙሉ ከመንግሥት ግምጃ ቤትና ከኤፍራጥስ ማዶ ከሚገኘው ገቢ ላይ ይከፈል።


ሌሎቹ ደግሞ እንዲህ አሉ፤ “የዕርሻችንንና የወይን ተክል ቦታችንን ግብር ለንጉሡ ለመክፈል ገንዘብ እስከ መበደር ደርሰናል።


እንዲህም እያሉ ይከስሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት፣ ለቄሳር ግብር እንዳይከፈል ሲከለክል፣ ደግሞም፣ ‘እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ’ ሲል አገኘነው።”


መምከር ከሆነ ይምከር፤ ለሌላቸው መለገስ ከሆነም አብዝቶ ይለግስ፤ ማስተዳደር ከሆነም በትጋት ያስተዳድር፤ ምሕረት ማድረግ ከሆነም በደስታ ይማር።


ስለዚህም ቅጣትን በመፍራት ብቻ ሳይሆን፣ ለኅሊና ሲባል ለባለሥልጣናት መገዛት ተገቢ ነው።


ለእያንዳንዱ የሚገባውን ስጡ፤ ግብር ከሆነ ግብርን፣ ቀረጥ ከሆነም ቀረጥን፣ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ ክብር ለሚገባውም ክብርን ስጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos