ሮሜ 11:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ምንድን ነው? እስራኤል የፈለገውን አላገኘም። የተመረጠው ግን አግኝቶአል፤ የቀሩትም ታወሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ምንድን ነው? እስራኤል አጥብቀው የፈለጉትን አላገኙትም፤ የተመረጡት ግን አገኙት፤ የቀሩትም ልባቸው ደነደነ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ምንድነው? እስራኤል የሚፈልጉትን አላገኙትም፤ የተመረጡት ግን አገኙት፤ የቀሩትም ደነዘዙ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ ውጤቱ ምን ሆነ? እስራኤላውያን የፈለጉትን አላገኙም፤ የተመረጡት ግን የፈለጉትን አገኙ፤ የቀሩት ልባቸውን አደነደኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ምንድር ነው? እስራኤል የሚፈልጉትን አላገኙትም፤ የተመረጡት ግን አገኙት፤ |
እነዚህ ሕዝቦች በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ ልባቸውን አደንድነዋልና፥ ጆሮአቸውንም ደፍነዋልና፥ ዐይኖቻቸውንም ጨፍነዋልና።
“በዐይናቸው አይተው፥ በልባቸውም አስተውለው እንዳይመለሱና እንዳልፈውሳቸው ዐይኖቻቸው ታወሩ፤ ልባቸውም ደነደነ።”
የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያውቁአትምና በራሳቸውም ጽድቅ ጸንተው ሊኖሩ ወደዱ፤ ለእግዚአብሔር ጽድቅ ግን መገዛት ተሳናቸው።
ወንድሞቻችን፥ እና ዐዋቂዎች ነን እንዳትሉ ይህን ምሥጢር ልታውቁ እወዳለሁ፦ አሕዛብ ሁሉ እስኪገቡ ድረስ ከእስራኤል እኩሌቶችን የልብ ድንቍርና አግኝቶአቸዋልና።
እንግዲህ ምን እንላለን? ከእነርሱ እንበልጣለን? አይደለም፤ አይሁዳዊንም፥ አረማዊንም እነሆ፥ አስቀድመን ነቅፈናቸዋል፤ ሁሉም ስተዋልና።
እንግዲህ ምን እንላለን? የኦሪትን ሕግ ከመሥራት ወጥተን ወደ እግዚአብሔር ጸጋ ስለ ገባን ኀጢአት እንሥራን? አይደለም።
ዳግመናም የክብሩን ባለጠግነት ሊያሳይ ቢወድ አስቀድሞ ለወደዳቸውና ለጠራቸው ለይቅርታ የተዘጋጁ የምሕረት መላእክትን ያመጣል።
ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ልባቸው ተሸፍኖአል፤ ያም መጋረጃ ብሉይ ኪዳን በተነበበት ዘመን ሁሉ ጸንቶ ኖሮአል፤ ክርስቶስ እስኪያሳልፈው ድረስ አልተገለጠምና።
እግዚአብሔርን የሚመስለው የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው የዚህ ዓለም አምላክ ልባቸውን አሳውሮአልና።
ነገር ግን ምን አለ? በየምክንያቱ በእውነትም ቢሆን፥ በሐሰትም ቢሆን፥ ስለ ክርስቶስ ይናገራሉ፤ ሰውንም ሁሉ ወደ እርሱ ይጠራሉ፤ በዚህም ደስ ብሎኛል፤ ወደፊትም ደስ ይለኛል።
ከዚያ በኋላ እንኳ በረከትን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና፤ በእንባም ተግቶ ምንም ቢፈልጋት ለንስሓ ስፍራ አላገኘምና።