ራእይ 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል፤ የውሃውም ሲሶ መራራ ሆነ፤ መራራም ስለተደረገ በውሃው ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኮከቡም ስም “እሬቶ” ይባል ነበር። የውሃውም አንድ ሦስተኛ መራራ ሆነ፤ ውሃው መራራ ከመሆኑ የተነሣም ብዙ ሰዎች ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል፤ የውሃውም ሲሶ መራራ ሆነ፤ መራራም ስለተደረገ በውሃው ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል፤ የውሃው አንድ ሦስተኛ መራራ ሆነ፤ መራራ በሆነውም ውሃ ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የውኃውም ሲሶ መራራ ሆነ መራራም ስለተደረገ በውኃው ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ። |
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኵሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና ሕማምን አበላቸዋለሁ፤ መራራ ውኃንም አጠጣቸዋለሁ።”
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ይህን ሕዝብ መከራን አበላዋለሁ፤ የሐሞትንም ውኃ አጠጣዋለሁ።
ፍርድን ወደ ቍጣ፥ የእውነትንም ፍሬ ወደ እሬት ለውጣችኋልና፥ በውኑ ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን? ወይስ በሬዎች በዚያ ላይ ያርሳሉን?
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
ሄዶ የእነዚያን አሕዛብ አማልክት ያመልክ ዘንድ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ልቡን ዛሬ የሚያስት ወንድ ወይም ሴት ወይም ወገን ወይም ነገድ አይኑርባችሁ፤ ሐሞትና እሬትም የሚያበቅል ሥር አይሁንባችሁ።
አስተውሉ፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ የሚያቃልል አይኑር፤ ሕማምን የምታመጣ፥ ብዙዎችንም የምታስታቸውና የምታረክሳቸው መራራ ሥር የምትገኝበትም አይኑር።
ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።
ፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።