ራእይ 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደሚያገሣ አንበሳም ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ በጮኸም ጊዜ የሰባቱ ነጐድጓዶች ድምፆች ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓዶች በየድምፃቸው ተናገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያገሣ የአንበሳን ድምፅ በመሰለ ታላቅ ድምፅም ጮኸ፤ በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓዶች ድምፃቸውን አሰሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጮኸም ጊዜ ሰባቱ ነጐድጓድ በየድምፃቸው ተናገሩ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛልና፥ “አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ እንደሚያገሣ፥ ድምፁም ተራሮችን እስኪሞላ በእርሱ ላይ እንደሚጮህ፥ እረኞችም ሁሉ ሲጮሁበት ከብዛታቸው የተነሣ እንደማይፈራ፥ ከድምፃቸውም የተነሣ እንደማይደነግጥ፥ እነርሱም ከቍጣው ብዛት የተነሣ ድል እንደሚሆኑና እንደሚደነግጡ፥ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይወጣል፤ ኀይለኛውንም ያጠፋል፤ ቅንአትንም ያስነሣል፤ በጠላቶቹም ላይ በኀይል ይጮኻል።
ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤ እንደ አንበሳ ደቦሎችም ይቆማሉ፤ ከጕድጓዱ እንደሚወጣ አውሬም ይነጥቃሉ፤ ይጮሃሉ፤ የሚድንም የለም።
“ስለዚህም ይህን ቃል ሁሉ ትንቢት ትናገርባቸዋለህ፤ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ እግዚአብሔር በላይ ሆኖ እንደ አንበሳ ያገሣል፤ በቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል፤ በበረቱ ላይ እጅግ ያገሣል፤ ወይንም እንደሚጠምቁ በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል።
የኪሩቤልም የክንፎቻቸው ድምፅ ሁሉን የሚችል አምላክ እንደሚናገረው ያለ ድምፅ እስከ ውጭው አደባባይ ድረስ በሩቅ ይሰማ ነበር።
ጌታ እግዚአብሔርን እከተለው ዘንድ እሄዳለሁ፤ እርሱ ያድነናልና፤ እርሱም እንደ አንበሳ ያገሣል፤ የውኃ ልጆችም ይደነግጣሉ።
እግዚአብሔርም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ይራራል፤ የእስራኤልንም ልጆች ያጸናል።
እንዲህም አለ፥ “እግዚአብሔር ከጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፤ ከኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ይሰጣል፤ የእረኞችም ማሰማሪያዎች ያለቅሳሉ፤ የቀርሜሎስም ራስ ይደርቃል።”
ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቍጣ በእነርሱ ስለሚፈጸም ኋለኛዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ታዩ።
ከአራቱም እንስሶች አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ የሚኖር የእግዚአሔር ቍጣ የሞላባቸውን ሰባት የወርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው።
ከዙፋኑም መብረቅና ድምፅ ነጐድጓድም ይወጣል፤ በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር፤ እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው።