ራእይ 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየውም ሁሉ መሰከረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት ያየውን ሁሉ መሰከረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክርነት፥ ላየውም ሁሉ መሰከረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሐንስም ስለ እግዚአብሔር ቃልና ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አስተማረው እውነት፥ እንዲሁም ስላየውም ነገር ሁሉ መሰከረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየውም ሁሉ መሰከረ። |
ስለዚህ ነገር ምስክር የሆነ፥ ስለ እርሱም ይህን የጻፈ ይህ ደቀ መዝሙር ነው፤ ምስክርነቱም እውነት እንደ ሆነ እኛ እናውቃለን።
እውነት እውነት እልሃለሁ፤ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፤ ነገር ግን ምስክርነታችንን አትቀበሉንም።
ነገር ግን ተነሣና በእግርህ ቁም፤ እኔን ባየህበትና ወደፊትም በምታይበት ነገር አገልጋይና ምስክር አድርጌ ልሾምህ ስለዚህ ተገልጬልሃለሁና።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔም ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በማባበልና ነገርን በማራቀቅ የእግዚአብሔርን ትምህርት ላስተምራችሁ የመጣሁ አይደለም።
ለድሜጥሮስ ሁሉ ይመሰክሩለታል፤ እውነት ራስዋም ትመሰክርለታለች፤ እኛም ደግሞ እንመሰክርለታለን፤ ምስክርነታችንም እውነት እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።
እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።
እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።
ዙፋኖችንም አየሁ፤ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ።