የባሕርን ኀይል አንተ ትገዛለህ፥ የሞገዱንም መናወጥ አንተ ዝም ታሰኘዋለህ።
ዐይኖቼም በሐዘን ፈዘዙ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ዘወትር ወደ አንተ እጣራለሁ፤ እጆቼንም ወደ አንተ ዘረጋሁ።
የሚያውቁኝን ከእኔ አራቅህ፥ በእነርሱ ዘንድ አጸያፊ አደረግኸኝ፥ ተዘግቶብኛል፥ መውጫም የለኝም።
ሐዘኔ ከመብዛቱ የተነሣ ዐይኖቼ ደከሙ፤ እግዚአብሔር ሆይ! በየቀኑ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ እጆቼንም ለጸሎት ወደ አንተ እዘረጋለሁ።
አንተ ልብህን ንጹሕ ብታደርግ፥ እጆችህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፥
“አሁንም፥ እነሆ፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፤ የሚያውቅልኝም በአርያም ነው።
ዐይኖች ከእንባ የተነሣ ፈዘዙ፥ ሁሉም እጅግ ተጸየፉኝ።
ሞት ለሰው ዕረፍቱ ነው፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ከለከለው።
ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘለዓለምም አይቈጣም።
መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው፥ በትናቸውም፤ ፍላጾችህን ላካቸው፥ አስደንግጣቸውም።
መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ፥ ከእጅህ ብርታት የተነሣ አልቄአለሁና።
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ልመናዬንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም አድምጥ፥ ቸልም አትበለኝ፤ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶችም ሁሉ እንግዳ ነኝና።
ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፤ እነርሱም ይምሩኝ፥ አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።
ዐይኔ ከቍጣ የተነሣ ታወከች፤ ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ አረጀሁ።
ቀንድና ጥፍር ካላበቀለ ከእምቦሳ ይልቅ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘዋለሁ።
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ ስለ አንቺ የተነገረው ነገር ድንቅ ነው።
አቤቱ፥ ምሕረትህን ለዘለዓለም እዘምራለሁ። ጽድቅህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ።
ጋሜል። እንዳልወጣ በዙሪያዬ ቅጥር ሠራብኝ፤ ሰንሰለቴንም አከበደ።
የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
ጌታችን ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ።