መዝሙር 82:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንድነት ተካክለው ተማክረዋልና፤ በአንተ ላይ ሤራ ቈረጡ፤ ቃል ኪዳንም አደረጉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዕውቀትም ማስተዋልም የላቸውም፤ በጨለማ ውስጥ ወዲያ ወዲህ ይመላለሳሉ፤ የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አያውቁም፥ አያስተውሉም፥ በጨለማ ውስጥ ይመላለሳሉ፥ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነርሱ ግን ምንም አያውቁም፤ አይገባቸውምም፤ በጨለማ ይመላለሳሉ፤ በዚህም ጊዜ የምድር መሠረትዋ እየተናወጠ ነው። |
የጠቢብ ዐይኖች በራሱ ላይ ናቸውና፤ አላዋቂ ግን በጨለማ ይሄዳል፤ ደግሞ የሁለቱም መጨረሻቸው አንድ እንደ ሆነ አስተዋልሁ።
የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፤ ተወዳጁ አዲስ ተክልም የይሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍርድን ያደርጋል ብየ እጠብቅ ነበር፤ እነሆም፥ ዐመፅን አደረገ፤ ጽድቅንም አይደለም፥ ጩኸትን እንጂ።
ስለዚህ ፍርድ ከእነርሱ ዘንድ ርቆአል፤ ጽድቅም አላገኛቸውም፤ ብርሃንን ሲጠባበቁ ብርሃናቸው ጨለማ ሆነባቸው፤ ብርሃንንም ሲጠባበቁ በጨለማ ሄዱ፤
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “ ገና ለጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው፤ በጨለማ የሚመላለስ የሚሄድበትን አያውቅምና ጨለማ እንዳያገኛችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤
እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን እንዲሁ እግዚአብሔር ይህን የማይገባውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው።
ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።