ሞትን እንሞታለንና፥ በምድርም ላይ እንደ ፈሰሰና እንደማይመለስ ውኃ እንሆናለንና፥ እግዚአብሔርም ነፍስን ይወስዳል። የተጣለውንም ከእርሱ ያርቅ ዘንድ ያስባል።
መዝሙር 77:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ አባቶቻቸው እንዳይሆኑ፥ ጠማማና የምታስመርር ትውልድ፥ ልብዋን ያላቀናች ትውልድ፥ መንፈስዋ በእግዚአብሔር ዘንድ ያልታመነች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሕረቱስ ለዘላለም ጠፋን? የገባውስ ቃል እስከ ወዲያኛው ተሻረን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ለዘለዓለም ይጥላልን? እንግዲህስ ቸርነቱን አይጨምርምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛን ማፍቀሩንስ ፈጽሞ ትቶአልን? ቃል ኪዳኑስ ከእንግዲህ ወዲህ አይጸናምን? |
ሞትን እንሞታለንና፥ በምድርም ላይ እንደ ፈሰሰና እንደማይመለስ ውኃ እንሆናለንና፥ እግዚአብሔርም ነፍስን ይወስዳል። የተጣለውንም ከእርሱ ያርቅ ዘንድ ያስባል።
ዘግይቶ ይደርቃል፤ በውስጡም ልምላሜ ሁሉ አይገኝም፤ ከቲኣሳ የምትመጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕዝቤ አልቅሱ፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና፤ ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
የሚያሳዝኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበረታሉ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ አልሽርም አለ? እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃም ሆነብኝ።
ምድሪቱን እንደ ሰለሉባቸው እንደ እነዚያ አርባ ቀኖች ቍጥር ስለ ኀጢአታችሁ ሁሉ አርባው ቀን አርባ ዓመት፥ አንዱ ቀንም አንድ ዓመት ይሁንባችሁ፤ እንግዲህ የቍጣዬን መቅሠፍት ታውቃላችሁ።
እግዚአብሔር እንደ ሰው የሚታለል አይደለም። እንደ ሰው ልጅም የሚዛትበት አይደለም፤ እርሱ ያለውን አያደርገውምን? አይናገረውምን? አይፈጽመውምን?
ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሓ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።