Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 27:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ዘግ​ይቶ ይደ​ር​ቃል፤ በው​ስ​ጡም ልም​ላሜ ሁሉ አይ​ገ​ኝም፤ ከቲ​ኣሳ የም​ት​መጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕ​ዝቤ አል​ቅሱ፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ውል ሕዝብ ነውና፤ ስለ​ዚህ ፈጣ​ሪው አይ​ራ​ራ​ለ​ትም፤ ሠሪ​ውም ምሕ​ረት አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ጫፎቿ ሲደርቁ ይሰበራሉ፤ ሴቶችም መጥተው ይማግዷቸዋል። ማስተዋል የሌለው ሕዝብ ስለ ሆነ፣ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ያበጀውም አይምረውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የዛፍ ቅርንጫፎች በሚደርቁበትም ጊዜ ይሰባበራሉ፤ ሴቶችም ለእሳት ማገዶ ይለቅሙአቸዋል፤ ሕዝቡ ማስተዋል ስለ ጐደለው ፈጣሪ አምላኩ አይራራለትም፤ ምንም ምሕረት አያደርግለትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፥ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 27:11
39 Referencias Cruzadas  

ሽመላ በሰ​ማይ ጊዜ​ዋን አው​ቃ​ለች፤ ዋኖ​ስና ጨረባ፥ ዋሊ​ያም የመ​ም​ጣ​ታ​ቸ​ውን ጊዜ ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍርድ አላ​ወ​ቁም።


ከማ​ኅ​ፀን የሠ​ራህ፥ የሚ​ቤ​ዥህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሁሉን ለብ​ቻዬ የፈ​ጠ​ርሁ፥ ሰማ​ያ​ትን የዘ​ረ​ጋሁ፥ ምድ​ር​ንም ያጸ​ናሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤


በስሜ የተ​ጠ​ራ​ውን ለክ​ብ​ሬም የፈ​ጠ​ር​ሁ​ትን፥ የሠ​ራ​ሁ​ት​ንና ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ሁሉ አምጣ” እለ​ዋ​ለሁ።


አሁ​ንም ያዕ​ቆብ ሆይ፥ የፈ​ጠ​ረህ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ፥ የሠ​ራህ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ በስ​ም​ህም ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ።


በሬ ገዢ​ውን አህ​ያም የጌ​ታ​ውን ጋጥ ዐወቀ፤ እስ​ራ​ኤል ግን አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ ሕዝ​ቤም አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ኝም።”


ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል።


ሁልጊዜ ኀጢአታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ አሕዛብ እንዲድኑ እንዳንናገራቸው ይከለክሉናልና። ነገር ግን ቍጣው ወደ እነርሱ ፈጽሞ ደርሶአል።


የማ​ያ​ስ​ተ​ውሉ፥ ዝን​ጉ​ዎች፥ ፍቅ​ርም፥ ምሕ​ረ​ትም የሌ​ላ​ቸው ናቸው።


በእኔ የማ​ይ​ኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅር​ን​ጫፍ ወደ ውጭ ይጥ​ሉ​ታል፤ ሰብ​ስ​በ​ውም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል።


የመንግሥትን ቃል ሰምቶ በማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው ይመጣል፤ በልቡ የተዘራውንም ይነጥቃል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።


በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዐይናቸውንም ጨፍነዋል፤’ የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።


አሁንስ ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቍኦረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።


ሕዝቤ አእ​ምሮ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ይመ​ስ​ላሉ፤ አን​ተም አእ​ም​ሮህ ተለ​ይ​ቶ​ሃ​ልና እኔ ካህን እን​ዳ​ት​ሆ​ነኝ እተ​ው​ሃ​ለሁ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ ረስ​ተ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ልጆ​ች​ህን እረ​ሳ​ለሁ።


ለና​ጌ​ብም ዱር እን​ዲህ በለው፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በአ​ንተ ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በው​ስ​ጥ​ህም ያለ​ውን የለ​መ​ለ​መ​ው​ንና የደ​ረ​ቀ​ውን ዛፍ ሁሉ ይበ​ላል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም ነበ​ል​ባል አይ​ጠ​ፋም፤ ከደ​ቡ​ብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ፊት ሁሉ ይቃ​ጠ​ል​በ​ታል።


“እኔም ደግሞ በዐ​ይኔ አል​ራ​ራም፤ ይቅ​ር​ታም አላ​ደ​ር​ግም፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንም በራ​ሳ​ቸው ላይ እመ​ል​ሳ​ለሁ” አለኝ።


የሕ​ዝቤ አለ​ቆች አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ እነ​ርሱ ሰነ​ፎች ልጆች ናቸው፤ ማስ​ተ​ዋ​ልም የላ​ቸ​ውም፤ ክፉ ነገ​ርን ለማ​ድ​ረግ ብል​ሃ​ተ​ኞች ናቸው፤ በጎ ነገ​ርን ማድ​ረግ ግን አያ​ው​ቁም።


የፈ​ጠ​ረህ ከማ​ኅ​ፀ​ንም የሠ​ራህ የሚ​ረ​ዳ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እን​ዲህ ይላል፥ “ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ህም ወዳጄ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ አት​ፍራ።


ሰው ሁሉ ክፉና በደ​ለኛ ነውና፥ አፍም ሁሉ ዐመ​ፅን ይና​ገ​ራ​ልና፥ ስለ​ዚህ ጌታ በጐ​ል​ማ​ሶ​ቻ​ቸው ደስ አይ​ለ​ውም፤ ለሙት ልጆ​ቻ​ቸ​ውና ለመ​በ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አይ​ራ​ራም። በዚህ ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


በአ​ለ​ቆ​ችም ላይ ኀሣር ፈሰሰ፥ መን​ገ​ድም በሌ​ለ​በት በም​ድረ በዳ አሳ​ታ​ቸው።


ጠብ​ቁት፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ ይህን ሥር​ዐት ሁሉ ሰም​ተው፦ እነሆ፥ ‘ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢ​ብና አስ​ተ​ዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአ​ሕ​ዛብ ፊት ጥበ​ባ​ች​ሁና ማስ​ተ​ዋ​ላ​ችሁ ይህ ነውና፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለማ​ወቅ ባል​ወ​ደዱ መጠን እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን የማ​ይ​ገ​ባ​ውን ይሠሩ ዘንድ ሰነፍ አእ​ም​ሮን ሰጣ​ቸው።


ስለ​ዚ​ህም ሕዝቤ ወደ ምርኮ ሄዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ወ​ቁ​ት​ምና፤ ብዙ​ዎቹ በረ​ኃ​ብና በውኃ ጥም ሞቱ፤


እርሱ ከመ​ከር በፊት አበባ በረ​ገፈ ጊዜ የወ​ይ​ንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወ​ይ​ኑን ቀጫ​ጭን ዘንግ በማ​ጭድ ይቈ​ር​ጣል፤ ጫፎ​ቹ​ንም ይመ​ለ​ም​ላል፤ ያስ​ወ​ግ​ድ​ማል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም​ሽን፦ በመ​ል​ካም ፍሬ የተ​ዋ​በ​ችና የለ​መ​ለ​መች የወ​ይራ ዛፍ ብሎ ጠራው፤ ከመ​ቈ​ረ​ጥ​ዋም ድምፅ የተ​ነሣ በላ​ይዋ እሳት ነደ​ደ​ባት፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ች​ዋም ተሰ​ብ​ረ​ዋል።


ሰው​ንና ወን​ድ​ሙን፥ አባ​ቶ​ች​ንና ልጆ​ችን በአ​ንድ ላይ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አል​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አላ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አል​ም​ራ​ቸ​ው​ምም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰላ​ሜን፥ ቸር​ነ​ቴ​ንና ምሕ​ረ​ቴን፥ ከዚህ ሕዝብ አስ​ወ​ግ​ጄ​አ​ለ​ሁና ልቅሶ ወዳ​ለ​በት ቤት አት​ግባ፤ ታለ​ቅ​ስና ታዝ​ንም ዘንድ አት​ሂድ።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ የተ​ነሣ የሰ​ላም ውበት ፈር​ሶ​አል።


ነገር ግን በመ​ዓት ተነ​ቀ​ለች፤ ወደ መሬ​ትም ተጣ​ለች፤ የሚ​ያ​ቃ​ጥ​ልም ነፋስ ፍሬ​ዋን አደ​ረቀ፤ ብር​ቱ​ዎች በት​ሮ​ች​ዋም ተሰ​በ​ሩና ደረቁ፤ እሳ​ትም በላ​ቻ​ቸው።


ወን​ዶ​ችም ደግሞ ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ይጫ​ወ​ታ​ሉና፥ ከጋ​ለ​ሞ​ቶ​ችም ጋር ይሠ​ዋ​ሉና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችሁ በሰ​ሰኑ ጊዜ፥ ሙሽ​ሮ​ቻ​ች​ሁም በአ​መ​ነ​ዘሩ ጊዜ አል​ቀ​ጣ​ኋ​ቸ​ውም፤ የማ​ያ​ስ​ተ​ው​ልም ሕዝብ ከአ​መ​ን​ዝራ ጋር ይቀ​ላ​ቀ​ላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios