መዝሙር 72:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥ ስለ ኀጢአታቸውም ጠፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክቡር ስሙ ለዘላለም ይባረክ፤ ምድርም ሁሉ በክብሩ ትሞላ። አሜን፤ አሜን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘለዓለም ይባረክ፥ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። አሜን፥ አሜን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክቡር ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን! ክብሩ በምድር ሁሉ ይሙላ! አሜን! አሜን! |
ሌዋውያኑም ኢያሱና ቀድምኤል፥ እንዲህ አሉ፥ “ቆማችሁ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላካችንን እግዚአብሔርን አመስግኑ። የከበረ ስሙንም አመስግኑ፤ በበረከትና በምስጋናም ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አድርጉት።”
እነርሱም አይጐዱትም፤ በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ማንንም አይጐዱም፤ አያጠፉምም፤ ብዙ ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
አንዱም ለአንዱ፥ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች” እያለ ይጮኽ ነበር።
ነቢዩም ኤርምያስ እንዲህ አለ፥ “አሜን፥ እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግ፤ የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ፥ ምርኮውንም ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ እግዚአብሔር የተናገርኸውን ትንቢት ይፈጽም።
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ርግማንንም የሚያመጣ ይህ ውኃ ወደ ሆድሽ ይግባ፥ ማኅፀንሽንም ይሰንጥቀው፤ ጎንሽም ይርገፍ። ሴቲቱም፦ ይሁን ይሁን ትላለች።
በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ “በረከትና ክብር ምስጋናም ኀይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን፤” ሲሉ ሰማሁ።