Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሚልክያስ 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “ከፀሓይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ፣ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናል፤ በየስፍራውም ሁሉ ለስሜ ዕጣንና ንጹሕ ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናልና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፤ በሁሉም ስፍራ ለስሜ ዕጣን ያመጣሉ፥ ንጹሕ ቁርባንም ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል ታላቅ ይሆናል፥” ይላል የሠራዊት ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፥ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ሚልክያስ 1:11
65 Referencias Cruzadas  

ፈጣ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ታዳ​ጊሽ ነው፤ እር​ሱም በም​ድር ሁሉ እን​ደ​ዚሁ ይጠ​ራል።


በፀ​ሐይ መው​ጫና በም​ዕ​ራብ ያሉ ከእኔ በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ያውቁ ዘንድ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነኝ፤ ከእ​ኔም ሌላ አም​ላክ የለም።


መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።


እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም፥ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሕዝቤን ከምሥራቅ ምድርና ከምዕራብ ምድር አድነዋለሁ፣


አቤቱ፥ እንደ ቸር​ነ​ትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ኀጢ​አ​ቴን ደም​ስስ።


ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል፤”


ልመ​ና​ዬን በፊቱ አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ መከ​ራ​ዬ​ንም በፊቱ እና​ገ​ራ​ለሁ።


ጢስ እን​ደ​ሚ​በ​ንን እን​ዲሁ ይብ​ነኑ፤ ሰም በእ​ሳት ፊት እን​ደ​ሚ​ቀ​ልጥ፥ እን​ዲሁ ኃጥ​ኣን ከአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይጥፉ።


እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቍጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሡ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ።


ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበ​ዛ​ል​ኝ​ማል፤ የመ​ዓዛ ሽታና የተ​ወ​ደደ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ስጦ​ታ​ች​ሁን ከአ​ፍ​ሮ​ዲጡ ተቀ​ብዬ አሟ​ል​ቻ​ለሁ።


በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግል ዘንድ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወን​ጌ​ልም እገዛ ዘንድ፥ በእኔ ትም​ህ​ርት አሕ​ዛብ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የተ​ወ​ደ​ደና የተ​መ​ረጠ መሥ​ዋ​ዕት ይሆኑ ዘንድ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕያ​ውና ቅዱስ፥ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኝም መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ጋ​ችሁ ታቀ​ርቡ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርኅ​ራኄ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። ይህም በዕ​ው​ቀት የሚ​ሆን አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ችሁ ነው።


ዕጣን በሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጊዜም ሕዝቡ በሙሉ በውጭ ይጸ​ልዩ ነበር።


እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።


በዚያን ጊዜም አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ስሙን እንዲጠሩ ንጹሕን ልሳን እመልስላቸዋለሁ።


እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፣ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል በአምላኩ በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፥ እነርሱም ይኖራሉ፥ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና።


ይኸ​ውም የቀሩ ሰዎ​ች​ንና ስሜም የተ​ጠ​ራ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ይፈ​ልጉ ዘንድ ነው” ይላል ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በም​ዕ​ራብ ያሉት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም፥ በፀ​ሐይ መው​ጫም ያሉት ክብ​ሩን ይፈ​ራሉ። መቅ​ሠ​ፍ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ ኀይ​ለኛ ፈሳሽ በቍጣ ይመ​ጣል።


ባሕር አየች፥ ሸሸ​ችም፥ ዮር​ዳ​ኖ​ስም ወደ​ኋ​ላው ተመ​ለሰ።


እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፤ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤


ዕጣ​ንም የተ​ሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወ​ርቅ ጭልፋ፤


ጠቢ​ባ​ንን ሲሞቱ ባየ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ እን​ደ​ዚሁ ልብ የሌ​ላ​ቸው ሰነ​ፎች ይጠ​ፋሉ፥ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ው​ንም ለሌ​ሎች ይተ​ዋሉ።


በተነ፥ ለች​ግ​ረ​ኞ​ችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዓለም ይኖ​ራል፤ ቀን​ዱም በክ​ብር ከፍ ከፍ ይላል።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ላ​ችሁ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ስሙ​ንም ጥሩ፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ክብ​ሩን አስ​ታ​ውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ አስ​ታ​ውሱ።


ታላቅ ሥራ ሠር​ቶ​አ​ልና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ዘምሩ፤ ይህ​ንም በም​ድር ሁሉ ላይ አስ​ታ​ውቁ።


“ሥራ​ቸ​ው​ንና አሳ​ባ​ቸ​ውን ዐው​ቄ​አ​ለሁ፤ እነ​ሆም እኔ እመ​ጣ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብ​ንና ልሳ​ና​ት​ንም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይመ​ጣሉ፤ ክብ​ሬ​ንም ያያሉ።


አቤቱ! እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስም​ህም በኀ​ይል ታላቅ ነው።


የአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ሆይ! በአ​ሕ​ዛብ ጥበ​በ​ኞች ሁሉ መካ​ከል፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ​ሌለ፥ ለአ​ንተ ክብር ይገ​ባ​ልና አን​ተን የማ​ይ​ፈራ ማን ነው?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ፥ ምስ​ጋ​ና​ውም ብዙ ነውና፤ በአ​ማ​ል​ክ​ትም ሁሉ ላይ የተ​ፈራ ነው።


መቃ​ብ​ራ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቤታ​ቸው ነው፥ ማደ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ለልጅ ልጅ ነው፤ በየ​ሀ​ገ​ራ​ቸ​ውም ስማ​ቸው ይጠ​ራል።


ነፍ​ሴን በሕ​ይ​ወት ያኖ​ራ​ታል፥ ለእ​ግ​ሮቼም ሁከ​ትን አል​ሰ​ጠም።


አቤቱ፥ ስለ ፍር​ድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይ​ሁ​ዳም ሴቶች ልጆች ሐሤት አደ​ረጉ፤


አቤቱ፥ አንተ እነሆ፥ የቀ​ድ​ሞ​ው​ንና የኋ​ላ​ውን ሁሉ ዐወ​ቅህ፤ አንተ ፈጠ​ር​ኸኝ፥ እጅ​ህ​ንም በላዬ አደ​ረ​ግህ።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ የታ​ወቀ ይሆ​ናል፤ በዚ​ያም ጊዜ ግብ​ፃ​ው​ያን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያው​ቃሉ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ትም ያቀ​ር​ቡ​ለ​ታል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስእ​ለት ይሳ​ላሉ፤ መባ​ኡ​ንም ያገ​ባሉ።


እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ይመ​ጣል፤ ቍጣ​ውም ከከ​ን​ፈ​ሮቹ ቃል ክብር ጋር ይነ​ድ​ዳል፤ ቃሉም ቍጣን የተ​መላ ነው፤ የቍ​ጣ​ውም መቅ​ሠ​ፍት እን​ደ​ም​ት​በላ እሳት ናት፤


ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ብሎ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነት፤ በጽ​ድ​ቅም ቢምል፥ አሕ​ዛብ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካሉ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።


እርሱም ብርን እንደሚያነጥርና እንደሚያጠራ ሰው ይቀመጣል፥ የሌዊንም ልጆች ያጠራል፥ እንደ ወርቅና እንደ ብርም ያነጥራቸዋል፣ እነርሱም ለእግዚአብሔር በጽድቅ ቍርባንን የሚያቀርቡ ይሆናሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios