ከክፉዎች ሴራ ከብዙዎች ዐመፅ አድራጊዎች ሰውረኝ።
ስለዚህ በመቅደስ ውስጥ አየሁህ፤ ኀይልህንና ክብርህንም ተመለከትሁ።
አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፥ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች በደረቅ መሬት፥ ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።
በመቅደስህ ውስጥ አንተን ተመለከትኩ፤ ኀይልህንና ክብርህንም አየሁ።
እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።
አቤቱ፥ ሕዝብህን በይቅርታህ ዐስበን፥ በማዳንህም ይቅር በለን፤
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ፥ በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ።
እንደ ሥራቸውና እንደ ዐሳባቸው ክፋት ስጣቸው፤ እንደ እጃቸውም ሥራ ክፈላቸው፤ ፍዳቸውን በራሳቸው ላይ መልስ።
ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፤ እነርሱም ይምሩኝ፥ አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።
አምላኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤ ለያዕቆብ መድኀኒትን ያዘዝህ።
አንተ በደልን የሚወድድ አምላክ አይደለህምና፤ ክፉዎች ከአንተ ጋር አያድሩም።
መዓትህን በላያቸው አፍስስ፥ የቍጣህ መቅሠፍትም ያግኛቸው።
ሰማያት የእርሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕዛብም ሁሉ ክብሩን አዩ።
የመቅደሴንም ስፍራ ያከብሩ ዘንድ የሊባኖስ ክብር፥ ጥዱና አስታው፥ ባርሰነቱም ወደ አንቺ ይመጣሉ፥
የካህናቱንም የሌዊን ልጆች ሰውነት ከፍ ከፍ አደርጋታለሁ፤ አረካታለሁ፤ ሕዝቤም ከበረከቴ ይጠግባል፥” ይላል እግዚአብሔር።