መዝሙር 59:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሕዝብህ ጭንቅን አሳየሃቸው፥ አስደንጋጩንም ወይን አጠጣኸን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ጨካኞች ያለ በደሌ፣ ያለ ኀጢአቴ በላዬ ተሰብስበው ዶለቱብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ፥ ከደም ሰዎችም አድነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዴት እንደ ሸመቁብኝ ተመልከት! እግዚአብሔር ሆይ! ምንም በደልና ኃጢአት ሳልሠራ ዐመፀኞች ሰዎች በእኔ ላይ ያሤራሉ። |
አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፥ ልመናዬንም አድምጥ፥ ልቅሶዬንም አድምጥ፥ ቸልም አትበለኝ፤ እኔ በምድር ላይ መጻተኛ ነኝና፥ እንደ አባቶችም ሁሉ እንግዳ ነኝና።
አቤቱ፥ የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ፥ ደስም ይበላቸው፤ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ፥ “ዘወትር እግዚአብሔር ታላቅ ነው” ይበሉ።
አንተ ግን እሽ አትበላቸው፤ ሊገድሉት ሽምቀዋልና፤ እስኪገድሉትም ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ እንዲህ የተማማሉ ሰዎች ከአርባ ይበዛሉ፤ አሁንም እስክትልክላቸው ይጠብቃሉ እንጂ እነርሱ ቈርጠዋል።”
ሳኦልም ለልጁ ለዮናታንና ለብላቴኖቹ ሁሉ ዳዊትን ይገድሉ ዘንድ ነገራቸው። የሳኦል ልጅ ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወድደው ነበር።
እነሆ፥ ዛሬ በዋሻው ውስጥ እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ እንደ ሰጠህ ዐይንህ አይታለች፤ አንተንም እንድገድልህ ሰዎች ተናገሩኝ፤ እኔ ግን፦ በእግዚአብሔር የተቀባ ነውና እጄን በጌታዬ ላይ አልዘረጋም ብዬ ራራሁልህ።
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት ይህን ቃል ለሳኦል መንገር በፈጸመ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድምፅህ ነውን?” አለ፤ ሳኦልም ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ።