መዝሙር 56:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አመሰግናለሁ፥ እዘምራለሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፋታቸው የተነሣ እንዳያመልጡ፣ ሕዝቦቹን በቍጣህ ጣላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሸምቁብኛል ይሸሸጋሉ፥ ተረከዜን ይከታተላሉ፥ ነፍሴንም ለማጥፋት ይጠብቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! በምንም መንገድ እንዲያመልጡ አታድርጋቸው! በቊጣህ ሕዝቦችን አዋርዳቸው። |
መንፈስን ለማስቀረት በመንፈሱ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞትም ቀን ሥልጣን የለውም፤ በጦርነትም ጊዜ ስንብት የለም፥ ኀጢአትም ሠሪውን አያድነውም።
እናንተም “ከሲኦል ጋር ተማምለናል፤ ከሞትም ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፤ ሐሰትንም መሸሸጊያን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና፥ ዐውሎ ነፋስም ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም” ትላላችሁና፥
ያዕቆብን በልተውታልና፥ አጥፍተውትማልና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ፥ ስምህንም በማይጠሩ ትውልድ ላይ መዓትህን አፍስስ።
መጥታችሁም ስሜ በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ብትቆሙ፦ ይህን አስጸያፊ የሆነ ነገርን ሁሉ ከማድረግ ተለይተናል ብትሉ፥
ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፥ ጠማምነትንም ትመለከት ዘንድ አትችልም፣ አታላዮችንስ ለምን ትመለከታለህ? ኃጢአተኛውስ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠው ስለምን ዝም ትላለህ?