Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 56:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 አምላክ ሆይ! በምንም መንገድ እንዲያመልጡ አታድርጋቸው! በቊጣህ ሕዝቦችን አዋርዳቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር ሆይ፤ ከክፋታቸው የተነሣ እንዳያመልጡ፣ ሕዝቦቹን በቍጣህ ጣላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ይሸምቁብኛል ይሸሸጋሉ፥ ተረከዜን ይከታተላሉ፥ ነፍሴንም ለማጥፋት ይጠብቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አቤቱ ልቤ ጽኑዕ ነው፥ አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 56:7
14 Referencias Cruzadas  

አምላክ ሆይ! አንተ ግን ክፉዎችን ወደ ጥልቅ ጒድጓድ ትጥላቸዋለህ፤ እነዚያ ነፍሰ ገዳዮችና ከዳተኞች ግማሽ ዕድሜአቸውን እንኳ አይኖሩም፤ እኔ ግን በአንተ እተማመናለሁ።


ዐይኖችህ እጅግ የጠሩ ስለ ሆኑ፥ ክፉ ነገርን መመልከት አይሆንላቸውም፤ አንተም ክፉ ነገር ሲሠራ ማየት አይስማማህም፤ ታዲያ እነዚህን ዐመፀኞችን እንዴት ዝም ብለህ ትመለከታቸዋለህ? ክፉዎችስ ከእነርሱ ይበልጥ ደጋግ የሆኑ ሰዎችን ሊያጠፉ ሲነሡ ስለምን ዝም ትላለህ?


ቊጣህን አንተን በማያውቁና ስምህን በማይጠሩ ሕዝቦች ላይ አፍስሰው፤ እነርሱ ሕዝብህን ፈጅተዋል፤ ሁላችንንም ፈጽመው በመደምሰስ፥ አገራችንን አውድመዋል።


እኔ የምጠላውን ይህን ሁሉ ነገር ከፈጸማችሁ በኋላ ወደ ቤተ መቅደሴ መጥታችሁ በፊቴ በመቆም ‘እኛ ከጥፋት ድነናል!’ ትላላችሁ።


“ከሞት ጋር ስምምነት አድርገናል፤ ከሙታንም ዓለም ጋር ቃል ኪዳን ገብተናል” እያላችሁ ትመካላችሁ፤ እንዲሁም “ማታለልን እንደ መጠለያ፥ ሐሰትንም እንደ መጠጊያ አምባ ስላደረግን መቅሠፍት በሚመጣበት ጊዜ ሳይነካን ያልፋል” ብላችሁ ተስፋ ታደርጋላችሁ።


የሕይወትን እስትንፋስ ለማስቀረትና የሞትን ቀን ለመለወጥ የሚችል ማንም የለም፤ ማንም ሰው ከጦር ሜዳ መሰናበት እንደማይችል ክፋትም ክፉ ሠሪዎችን አይለቃቸውም።


ልባቸው የክፋት ማደሪያ ስለ ሆነ በጠላቶቼ ላይ ድንገተኛ ሞት ይምጣባቸው! በሕይወት ሳሉ ወደ ሙታን ዓለም ይውረዱ!


እግዚአብሔር ሆይ! በከተማይቱ ውስጥ ዐመፅንና ብጥብጥን ስላየሁ፥ የክፉዎችን ምክር አጥፋ፤ ዕቅዳቸውንም ደምስስ!


ክፉዎች እንዴት እንደ ወደቁ እይ። እነሆ ተጥለዋል፤ መነሣትም አይችሉም።


ክፉ ሰው በጻድቁ ላይ ይሸምቃል፤ ሊገድለውም ይፈልጋል።


እንዲሁም በሀብታቸው ብዛት የሚተማመኑና በብልጽግናቸው ብዛት የሚመኩ ክፉ ሰዎች ቢከቡኝስ ለምን እፈራለሁ?


ምንም በደል ሳልሠራ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተዋል፤ ይህን ተመልከትና ተነሥተህ እርዳኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios