ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ጠላቶች ረገጡኝ፥ የሚዋጉኝ በዝተዋልና ፈራሁ።
ወደ እኔ ተመልከት፤ መልስልኝም። በውስጤ ታውኬአለሁ፤ ተናውጬአለሁም፤
አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥ ልመናዬንም ቸል አትበል።
የልቤ ጭንቀት ሰላም ስላልሰጠኝ እባክህ፥ አድምጠህ መልስ ስጠኝ።
አቤቱ፥ በኀይሌ እወድድሃለሁ።
አዲስ ምስጋናንም አመስግኑት፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩለት፤
ሰው ሁሉ እንደ ጥላ ይመላለሳል፥ ነገር ግን በከንቱ ይታወካሉ። ያከማቻሉ የሚሰበስቡለትንም አያውቁም።
እጅህ ጠላትን አጠፋች፥ እነርሱንም ተከልህ፤ አሕዛብን አሠቃየኻቸው፥ አሳደድኻቸውም።
አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም በኢየሩሳሌም ጸሎት ይቀርባል።
የሰማነውንና ያየነውን፥ አባቶቻችንም የነገሩንን፥ ለሚመጣ ትውልድ ከልጆቻቸው አልሰወሩም።
እንደ ሸመላ እንዲሁ ጮህሁ፤ እንደ ርግብም አጕረመረምሁ፤
እንደ ድብና እንደ ርግብ በአንድነት ይሄዳሉ፤ ፍርድን እንጠባበቅ ነበር፤ መዳንም የለም፤ ከእኛም ርቆአል።
አንተ ድምፄን ሰማህ፤ ጆሮህንም ከልመናዬ አትመልስ።