ፍርሃትና እንቅጥቅጥ ያዙኝ፥ ጨለማም ሸፈነኝ።
የገዛ ክፋታቸው በሚያደቡብኝ ላይ ይመለስባቸው፤ በቃልህ ታማኝ ነህና አጥፋቸው።
እንግዶች ተነሥተውብኛልና፥ ጨካኞችም ነፍሴን ሽተዋታልና። እግዚአብሔርን በፊታቸው አላደረጉትም።
ተንኰላቸውን በሚያስጨንቁኝ ጠላቶቼ ላይ መልስባቸው፤ እነርሱን በማጥፋት ታማኝነትህን አሳይ።
እግዚአብሔርም ይበቀልልኛል፤ አቤቱ፥ ምሕረትህ ለዘለዓለም ነው፤ አቤቱ የእጅህን ሥራ ቸል አትበል።
ለእጆቼ ጠብን፥ ለጣቶቼም ሰልፍን ያስተማራቸው አምላኬ እግዚአብሔር ይመስገን፤
ልጆቻቸው በጐልማስነታቸው እንደ አዲስ ተክል የሆኑ፥ ሴቶች ልጆቻቸውም እንደ እልፍኝ ያማሩና ያጌጡ፤
አቤቱ፥ በጽድቅህ ምራኝ፤ ስለ ጠላቶቼ መንገዴን በፊትህ አቅና።
የናስ አንጥረኛው እስክንድሮስ እጅግ ከፋብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይመልስለታል።
እርስዋ እንደ ሰጠች መጠን ብድራት መልሱላት፤ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤