መዝሙር 53:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፋትን ወደ ጠላቶች ይመልሳታል፤ በእውነትህም አጥፋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚያስፈራ ነገር በሌለበት፣ በዚያ፣ ድንጋጤ ውጧቸዋል፤ እግዚአብሔር የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት በተነ፤ እርሱ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው፣ አንተ አሳፈርሃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንጀራ እንደሚበላ ሕዝቤን የሚበሉ ግፍ አድራጊዎች ሁሉ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የሕዝቡን ጠላቶች ስለ ሰባበራቸው ከምንጊዜውም ይልቅ በፍርሃት ተጨነቁ፤ እግዚአብሔርም ስለ ጠላቸው ፈጽሞ ያፍራሉ። |
ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘለዓለም አይታወክም።
ዋው። ማደሪያውን እንደ ወይን ጋረደ፤ በዓሉን ሁሉ አጠፋ፤ እግዚአብሔር በጽዮን ያደረገውን በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፤ በቍጣውም መዓት ነገሥታቱን፥ አለቆቹንና ካህናቱን አጠፋ።
የእስራኤልንም ልጆች ሬሳዎች በጣዖቶቻቸው ፊት አኖራለሁ፤ አጥንቶቻችሁንም በመሠዊያዎቻችሁ ዙሪያ እበትናለሁ።
ፊቴንም አከብድባችኋለሁ፤ በጠላቶቻችሁም ፊት ትወድቃላችሁ፤ የሚጠሏችሁም ያሸንፉአችኋል። ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።
በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች፤ ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ ፤
በሰፈሩና በእርሻውም ድንጋጤ ሆነ፤ በሰፈሩ የተቀመጡ ሕዝብና የሚዋጉትም ሁሉ ተሸበሩ፤ መዋጋትም አልቻሉም፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ታላቅ ድንጋጤ መጣ።