መዝሙር 53 - አዲሱ መደበኛ ትርጒምመዝሙር 53 53፥1-6 ተጓ ምብ – መዝ 14፥1-7 ለመዘምራን አለቃ፤ በማኸላት፤ የዳዊት ማስኪል። 1 ሞኝ በልቡ፣ “እግዚአብሔር የለም” ይላል። ብልሹዎች ናቸው፤ ተግባራቸውም ጸያፍ ነው፤ በጎ ነገር የሚሠራ አንድ እንኳን የለም። 2 የሚያስተውል፣ እግዚአብሔርን የሚፈልግ እንዳለ ለማየት፣ እግዚአብሔር ከሰማይ ወደ ሰው ልጆች ተመለከተ። 3 ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር አሉ፤ በአንድነትም ተበላሹ፤ መልካም የሚያደርግ የለም፤ አንድ እንኳ። 4 ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉት፣ እግዚአብሔርንም የማይጠሩት፣ እነዚህ ክፉ አድራጊዎች ምንም አያውቁምን? 5 የሚያስፈራ ነገር በሌለበት፣ በዚያ፣ ድንጋጤ ውጧቸዋል፤ እግዚአብሔር የዘመቱብህን ሰዎች ዐጥንት በተነ፤ እርሱ እግዚአብሔር ስለ ናቃቸው፣ አንተ አሳፈርሃቸው። 6 ምነው ለእስራኤል የሚሆን መዳን ከጽዮን በወጣ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣ ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤልም ሐሤት ያድርግ። |
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አዲሱ መደበኛ ትርጕም™
የቅጂ መብት © 2001, 2024 በBiblica, Inc.
በፈቃድ የሚወሰድ። በዓለም ዐቀፍ ባለቤትነቱ።
The Holy Bible, New Amharic Standard Version™
Copyright © 2001, 2024 by Biblica, Inc.
Used with permission. All rights reserved worldwide.
Biblica, Inc.