መዝሙር 50:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኀጢአቴም አንጻኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍጹም ውብ ከሆነችው ከጽዮን፣ እግዚአብሔር አበራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጽዮን፥ ከውበት ሙላቱ እግዚአብሔር ያበራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በውበትዋ ፍጹም ከሆነችው ከጽዮን ከተማ የደመቀ ብርሃንን ያበራል። |
ጕሮሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለንተናውም የተወደደ ነው፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ልጅ ወንድሜ ይህ ነው፥ ወዳጄም ይህ ነው።
እነሆ፥ እግዚአብሔር በምድር በሚኖሩት ላይ ከመቅደሱ መቅሠፍቱን ያመጣል፤ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፤ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም።
ሳምኬት። መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል፦ “በውኑ የምድር ሁሉ ደስታ፥ አክሊልና ክብር የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፤ ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ።
እንዲህም አለ፦ “እግዚአብሔር ከሲና መጣ፤ በሴይርም ተገለጠልን፤ ከፋራን ተራራ፥ ከቃዴስ አእላፋት ጋር ፈጥኖ መጣ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር በቀኙ ነበሩ።