Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 50:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እኔ በደ​ሌን አው​ቃ​ለ​ሁና፥ ኀጢ​አ​ቴም ሁል​ጊዜ በፊቴ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አምላካችን ይመጣል፤ ዝምም አይልም፤ የሚባላ እሳት በፊቱ፣ የሚያስፈራ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፥ እሳት በፊቱ ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ ነፋስ አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አምላካችን ይመጣል፤ ዝም አይልም፤ የሚያቃጥል እሳት በፊቱ ነው፤ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስም በዙሪያው ነው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 50:3
28 Referencias Cruzadas  

እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥታ ያጥኑ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች በላች።


እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥቶ በላ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ሞቱ።


መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


ይህን የሚመሰክር “አዎን በቶሎ እመጣለሁ፤” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ!ጅ ና።


አም​ላ​ካ​ችን በእ​ው​ነት የሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነውና።


እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል።


የኀ​ያ​ላን አም​ላክ ሆይ፥ ማደ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ እጅግ የተ​ወ​ደዱ ናቸው።


ሰው​ነቴ ስድ​ብ​ንና ውር​ደ​ትን ታገ​ሠች፤ አዝኜ ተቀ​መ​ጥሁ፥ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ኝ​ም አጣሁ።


እንደ በጎች ሞት በሲ​ኦል ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል፥ ቅኖ​ችም በማ​ለዳ ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፥ ረድ​ኤ​ታ​ቸ​ውም ከክ​ብ​ራ​ቸው ተለ​ይታ በሲ​ኦል ትጠ​ፋ​ለች።


አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ እን​ዲ​ያ​ልፍ ዛሬ ዕወቅ፤ እርሱ የሚ​በላ እሳት ነው፤ እርሱ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ በፊ​ት​ህም ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ነገ​ረህ ከፊ​ትህ ያር​ቃ​ቸ​ዋል፥ ፈጥ​ኖም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ሳት ስለ ወረ​ደ​በት የሲና ተራራ ሁሉ እንደ ምድጃ ጢስ ይጤስ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም ሁሉ እጅግ ይና​ወጥ ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጽ​መው ደነ​ገጡ።


እኛስ እን​ዲህ ያለ​ውን ታላቅ መዳን ቸል ብን​ለው እን​ዴት እና​መ​ል​ጣ​ለን? ይህ በጌታ በመ​ጀ​መ​ሪያ የተ​ነ​ገረ ነበ​ረና የሰ​ሙ​ትም ለእኛ አጸ​ኑት።


እና​ንተ አእ​ምሮ የሌ​ላ​ችሁ፥ ልቡ​ና​ች​ሁን አረ​ጋጉ፤ ጽኑ፤ አት​ፍሩ፤ እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችን ፍር​ድን ይመ​ል​ሳል፤ ይበ​ቀ​ላ​ልም፤ እር​ሱም መጥቶ ያድ​ነ​ናል።


እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከሰ​ሜን በኩል ዐውሎ ነፋ​ስና ታላቅ ደመና፥ የሚ​በ​ር​ቅም እሳት መጣ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ፀዳል ነበረ፤ በመ​ካ​ከ​ልም በእ​ሳቱ ውስጥ የሚ​ብ​ለ​ጨ​ለጭ ነገር ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios