መዝሙር 49:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቤትህ ፍሪዳን፥ ከመንጋህም ጊደርን አልወስድም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም ዘላለም ይኖራል፣ መበስበስንም አያይም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የነፍሳቸው ዋጋ ክቡር ነው፥ መቼውንም በቂ አይሆንም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዳይሞትና ወደ መቃብር እንዳይወርድ፥ ለዘለዓለም እንዲኖር ለማድረግ የቱንም ያኽል ቢከፈል በቂ አይሆንም። |
በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች። ጻድቅ በሞተ ጊዜ ጸጸትን ይተዋል፥ የኀጢአተኛ ሞት ግን በእጅ የተያዘና ሣቅ ይሆናል።
መንፈስን ለማስቀረት በመንፈሱ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞትም ቀን ሥልጣን የለውም፤ በጦርነትም ጊዜ ስንብት የለም፥ ኀጢአትም ሠሪውን አያድነውም።
በሁለተኛው መዝሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ’ እንዳለ ኢየሱስን አስነሥቶ ተስፋውን ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአል።
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ እንደሚነሣ፥ ሥጋዉም በመቃብር እንደማይቀር፥ ጥፋትንም እንደማያይ አስቀድሞ ዐውቆ ተናገረ።