Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 13:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በሁ​ለ​ተ​ኛው መዝ​ሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ’ እን​ዳለ ኢየ​ሱ​ስን አስ​ነ​ሥቶ ተስ​ፋ​ውን ለእኛ ለል​ጆ​ቻ​ቸው ፈጽ​ሞ​አል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ኢየሱስንም ከሙታን በማስነሣቱ ለእነርሱ የገባውን ቃል ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሟል፤ ይኸውም እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር እንዲህ ብሎ ተጽፏል፤ “ ‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 እግዚአብሔር ኢየሱስን ከሞት በማስነሣቱ ይህንኑ ተስፋ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞታል፤ ይህም በሁለተኛው መዝሙር፥ ‘አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ፤’ ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ ‘አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ’ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 13:33
10 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እና​ገር ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለኝ፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ።


ከሙ​ታን በተ​ነሣ ጊዜም ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ስለ​ዚህ እንደ ነገ​ራ​ቸው ዐሰቡ፤ በመ​ጻ​ሕ​ፍት ቃልና ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በነ​ገ​ራ​ቸ​ውም ነገር አመኑ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው።


መፍ​ረስ መበ​ስ​በ​ስ​ንም እን​ዳ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙ​ታን ለይቶ እን​ዳ​ስ​ነ​ሣው እን​ዲህ አለ፦ ‘የታ​መ​ነ​ውን የዳ​ዊ​ትን ቅዱስ ተስፋ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


ይህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያስ​ነ​ሣው ግን መፍ​ረስ መበ​ስ​በ​ስን አላ​የም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን የሞ​ትን ማሰ​ሪያ ፈቶ ከሙ​ታን ለይቶ አስ​ነ​ሣው፤ ሞት እር​ሱን ሊይ​ዘው አይ​ች​ል​ምና።


እር​ሱን ኢየ​ሱ​ስን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ነ​ሣው፤ ለዚ​ህም እኛ ሁላ​ችን ምስ​ክ​ሮቹ ነን።


ወዲ​ያ​ው​ኑም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነው” ብሎ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በየ​ም​ኵ​ራ​ቦቹ ሰበከ፥ አስ​ተ​ማ​ረም።


እን​ዲሁ ክር​ስ​ቶ​ስም ሊቀ ካህ​ናት ይሆን ዘንድ ራሱን ያከ​በረ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን፥ “አንተ ልጄ ነህ፥ እኔም ዛሬ ወለ​ድ​ሁህ” ያለው እርሱ ራሱ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos