ሕዝቤ፥ ስማኝ ልንገርህ፤ እስራኤልም እመሰክርብሃለሁ፤ አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ።
የሌላውን ሕይወት መቤዠት የሚችል ሰው፣ ወይም ለእግዚአብሔር ወጆ የሚከፍልለት ማንም የለም።
በኃይላቸው የሚታመኑ፥ በሀብታቸውም ብዛት የሚመኩ፥
ሰው ራሱን መቤዠትም ሆነ ለሕይወቱ ቤዛ የሚሆነውን ዋጋ ለእግዚአብሔር መክፈል አይችልም።
የባለጠጋ ሰው ሀብቱ የጸናች ከተማ ናት፥ ክብሯም እንደ ትልቅ ጥላ ታጠላለች።
የሰዎቻችሁም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል።
ኤፍሬምም፥ “ባለጸጋ ሆኜአለሁ፤ ሀብትንም አግኝቻለሁ፤ በድካሜም ሁሉ ኀጢአት የሚሆን በደል አይገኝብኝም” አለ።
ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?
እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”
ልባሞቹ ግን መልሰው ‘ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ፤’ አሉአቸው።
ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?
ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፤ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤
ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።