መዝሙር 44:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘለዓለም ነው፤ በትረ መንግሥትህ የጽድቅ በትር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቀስቴ አልተማመንም፤ ሰይፌም አያስጥለኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን፥ በስምህም የሚነሡብንን እንረግጣለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቀስቴ አልተማመንም፤ ሰይፌም አያድነኝም። |
እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን በአነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርግ ነበር ፤ እጁንም በአወረደ ጊዜ ዐማሌቅ ድል ያደርግ ነበር።
ነገር ግን የይሁዳን ልጆች ይቅር እላቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸውም እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ እንጂ በቀስት ወይም በሰይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠረገላ፥ ወይም በፈረሶች፥ ወይም በፈረሰኞች የማድናቸው አይደለም” አለው።
ይህም ጉባኤ ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍና በጦር የሚያድን እንዳይደለ ያውቃል። ሰልፉ ለእግዚአብሔር ነውና፤ እግዚአብሔርም እናንተን በእጃችን አሳልፎ ይሰጣል።”