እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
መዝሙር 44:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል። የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝብህን በርካሽ ዋጋ ሸጥኸው፤ ከሽያጩም ያገኘኸው ትርፍ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ በጎች ሊበሉን ሰጠኸን፥ ወደ አሕዛብም በተንኸን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝብህን በአነስተኛ ዋጋ ሸጥከው፤ እርሱንም በመሸጥ ምንም አላተረፍክም። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ደብዳቤ የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢአታችሁ ተሸጣችኋል፤ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ በሄዳችሁበትም ሁሉ ሰይፍ ታጠፋችኋለች፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፤ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ።
አንዱ ሽሁን እንዴት ያሳድዳቸዋል? ሁለቱስ ዐሥሩን ሽህ እንዴት ያባርሩአቸዋል? እግዚአብሔር ፍዳውን አምጥቶባቸዋልና። አምላካችንም አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና።
እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፤ እግዚአብሔር በውስጣቸው በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከልም በቍጥር ጥቂቶች ሆናችሁ ትቀራላችሁ።
ቀረፋም፥ ቅመምም፥ የሚቃጠልም ሽቱ፥ ቅባትም፥ ዕጣንም፥ የወይን ጠጅም፥ ዘይትም፥ የተሰለቀ ዱቄትም፥ ስንዴም፥ ከብትም፥ በግም፥ ፈረስም፥ ሰረገላም፥ ባሪያዎችም፥ የሰዎችም ነፍሳት ነው።
እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ተቈጣ፤ ወደ ማረኳቸውም ማራኪዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ማረኩአቸውም፤ በዙሪያቸውም ባሉት በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ከዚያም ወዲያ ጠላቶቻቸውን ሊቋቋሙ አልቻሉም።
ስለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በወንዞችም መካከል ባለች በሶርያ ንጉሥ በኩሳርሳቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የእስራኤልም ልጆች ለኩሳርሳቴም ስምንት ዓመት ተገዙለት።