መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ፥ ከእጅህ ብርታት የተነሣ አልቄአለሁና።
ልቤ በኀይል ይመታል፤ ጕልበት ከድቶኛል፤ የዐይኔም ብርሃን ጠፍቷል።
አቤቱ፥ ፈቃዴ ሁሉ በፊትህ ነው፥ ጭንቀቴም ከአንተ አይሰወርም።
ልቤ በፍጥነት ይመታል፤ ኀይሌም ደክሞአል፤ ዐይኖቼም ብርሃን አጥተዋል።
የኃጥኣን መቅሠፍታቸው ብዙ ነው፤ በእግዚአብሔር የሚታመኑትን ግን ይቅርታ ይከባቸዋል።
አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥ ከጽድቅ ከወጡ ሕዝብም በቀሌን ተበቀል። ከዐመፀኛና ከሸንጋይ ሰው አድነኝ።
ዐይኔ ከቍጣ የተነሣ ታወከች፤ ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ አረጀሁ።
እሰይ! እሰይ! የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።
የባሕርን ኀይል አንተ ትገዛለህ፥ የሞገዱንም መናወጥ አንተ ዝም ታሰኘዋለህ።
ልቤ ሳተ፤ ኀጢአቴም አሰጠመኝ፤ ሰውነቴም ደነገጠብኝ።
ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእንባ ደከመች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በምድር ላይ ተዋረደ።