መዝሙር 33:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃኑ፥ ጆሮቹም ወደ ልመናቸው ናቸውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ የሁሉን ልብ የሠራ፣ የሚያደርጉትን ሁሉ የሚያስተውል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ብቻውን ልባቸውን የሠራ ሥራቸውንም ሁሉ የሚያስተውል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሁላቸውንም ልብ የሠራ እርሱ ነው የሚያደርጉትን ሁሉ ይመለከታል። |
እነሆ፥ ይህን አላውቅም ብትል፥ እግዚአብሔር የሁሉን ልብ እንዲያውቅ ዕወቅ። ለሁሉ እስትንፋስን የፈጠረ እርሱ ሁሉን ያውቃል። ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፍለዋል።
እግዚአብሔር በጊዜው ሰዎችን ቅኖች አድርጎ እንደ ሠራቸው እነሆ፥ ይህን ብቻ አገኘሁ፥ እነርሱ ግን ብዙ ዕውቀትን ይሻሉ።
እግዚአብሔር በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ስምህ ታላቅ የሆነ፥ ኀያል፥ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዐይኖችህ በሰው ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።
ወንጀላቸውን አንድ ያደርጉ ዘንድ በልባቸው እንደ አሰቡ ክፋታቸውን ሁሉ ዐሰብሁ፤ አሁንም ክፋታቸው ከብባቸዋለች፤ በደላቸውም በፊቴ አለች።
እርሱም በምድር ሁሉ ላይ ይኖሩ ዘንድ ሰዎችን ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ ይኖሩባትም ዘንድ ዘመንንና ቦታን ወስኖ ሠራላቸው።
ጊዜው ሳይደርስ ዛሬ ለምን ትመረምራላቸሁ? በጨለማ ውስጥ የተሰወረውንም የሚያበራ፥ የልብን አሳብም የሚገልጥ ጌታችን ይመጣል፤ ያንጊዜ ሁሉም ዋጋውን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።