ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤ አንተ በከንቱ የሚጠሉኝን ሁሉ መትተሃልና፥ የኃጥኣንንም ጥርስ ሰብረሃልና።
እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ! አምላኬ ሆይ፤ ታደገኝ፤ የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህ፤ የክፉዎችንም ጥርስ ትሰባብራለህ።
የሚከቡኝን አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
ጌታ ሆይ! ተነሥ! አምላኬ ሆይ! መጥተህ አድነኝ! የጠላቶቼን መንጋጋ ስበር፤ ጥርሶቻቸውንም አድቅቅ።
ከዚያም ጦሩ በሀገሩ ሁሉ ፊት ተበተነ፤ በዚያም ቀን በሰይፍ ከተገደሉት ሕዝብ ይልቅ በበረሓ የሞቱ ይበዛሉ።
በቍጣው ጣለኝ፤ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፤ ፍላጻዎቹንም በእኔ ላይ ፈተነ።
የኀጢአተኞችን መንጋጋ ሰበርሁ፥ የነጠቁትንም ከጥርሳቸው ውስጥ አስጣልሁ።
እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል።
ከኃጥኣን ጋር ነፍሴን አትውሰዳት፤ ክፋትም በልባቸው እያለ ከባልንጀራቸው ጋር ሰላምን ከሚናገሩ ዐመፅ አድራጊዎች ጋር አትጣለኝ።
ማታ ይመለሱ እንደ ውሾችም ይራቡ፥ በከተማም ይዙሩ።
ወዳጆችህም፥ እንዲድኑ በቀኝህ አድን፥ ስማኝም።
አቤቱ፥ ተመለስ ነፍሴንም አድናት፥ ስለ ቸርነትህም አድነኝ።
አቤቱ፥ በመዓትህ ተነሥ፤ በጠላቶቼ ላይ ተነሣባቸው፤ አቤቱ፥ አምላኬ፥ ባዘዝኸው ሥርዐት ተነሥ።
እግዚአብሔር ይቅርታን ይረሳልን? በቍጣውስ ምሕረቱን ዘጋውን?
ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ የክንድሽንም ኀይል ልበሺ፤ እንደ ቀድሞውም ዘመን እንደ ጥንቱ ትውልድ ተነሺ።
ጕንጩን ለሚመታው ይሰጣል፤ ስድብንም ይጠግባል።
እንጨቱን፦ ንቃ፥ ዲዳውንም ድንጋይ፦ ተነሣ ለሚለው ወዮለት! በውኑ ይህ ያስተምራልን? እነሆ፥ በወርቅና በብር ተለብጦአል፥ ምንም እስትንፋስ የለበትም።