መዝሙር 23:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆቹም የነጹ፥ በነፍሱ ላይ ከንቱን ያልወሰደ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ፣ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንህ፣ ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ፣ እነርሱ ያጽናኑኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፥ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጣም ጨለማ በሆነ ሸለቆ በኩል ባልሄድም እንኳ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንክ፥ ምንም ክፉ ነገር አልፈራም። ያንተ በትርና ምርኲዝ ያጽናኑኛል። |
ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘለዓለም አይታወክም።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
እነርሱም፥ “ከግብፅ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳና በባድማ፥ ዕንጨትና ውኃ፥ የእንጨት ፍሬም በሌለበት ምድር፥ ሰው በማያልፍበትና የሰው ልጅም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም።
በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።