Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘካርያስ 11:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በይሁዳና በእስራኤል መካከል ያለውንም ወንድማማችነት እሰብር ዘንድ ማሰሪያ የተባለቸውን ሁለተኛይቱን በትሬን ቈረጥሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከዚያም የእስራኤልንና የይሁዳን ወንድማማችነት በማፍረስ፣ “አንድነት” ብዬ የጠራሁትን ሁለተኛውን በትሬን ሰበርሁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ከዚያም በይሁዳና በእስራኤል መካከል ያለውንም ወንድማማችነት ለመለያየት “አንድነት” የተባለቸውን ሁለተኛይቱን በትሬን ሰበርኳት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚህ በኋላ “አንድነት” የተባለውን ሁለተኛውን በትር ሰበርኩት፤ ይህንንም ማድረጌ በይሁዳና በእስራኤል መካከል የነበረው ወንድማማችነት መጥፋቱን ለማመልከት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በይሁዳና በእስራኤል መካከል ያለውንም ወንድማማችነት እሰብር ዘንድ ማሰሪያ የተባለቸውን ሁለተኛይቱን በትሬን ቈረጥሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 11:14
14 Referencias Cruzadas  

እያ​ን​ዳ​ን​ዱም የክ​ን​ዱን ሥጋ ይበ​ላል፤ ምናሴ ኤፍ​ሬ​ምን፥ ኤፍ​ሬ​ምም ምና​ሴን ይበ​ላል፤ እነ​ርሱ በአ​ን​ድ​ነት የይ​ሁዳ ጠላ​ቶች ይሆ​ና​ሉና። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ አሉና።


ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ፤ በእውነትም ላይ አትዋሹ።


እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​በ​ላ​ሉና የም​ት​ነ​ካ​ከሱ ከሆነ ግን፥ እርስ በር​ሳ​ችሁ እን​ዳ​ት​ተ​ላ​ለቁ ተጠ​ን​ቀቁ።


በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፤ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤


እኔም፦ እናንተን አልጠብቅም፣ የሚሞተው ይሙት፥ የሚጠፋውም ይጥፋ፣ የቀረውም እያንዳንዱ የባልንጀራውን ሥጋ ይብላ አልሁ።


እኔም ለእርድ የሚሆኑትን በጎች፥ የመንጋውን ችግረኞች ጠበቅሁ። ሁለት በትሮችንም ወሰድሁ፣ የአንዲቱን ስም ውበት የሁለተኛይቱንም ስም ማሰሪያ ብዬ ጠራሁ፣ መንጋውንም ጠበቅሁ።


የኤ​ፍ​ሬ​ምም ቅናት ይሻ​ራል፤ የይ​ሁ​ዳም ጠላ​ቶች ይጠ​ፋሉ፤ ኤፍ​ሬ​ምም በይ​ሁዳ አይ​ቀ​ናም፤ ይሁ​ዳም ኤፍ​ሬ​ምን አያ​ስ​ጨ​ን​ቅም።


ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖሩ አልራራም፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እነሆም፥ ሰውን ሁሉ በባልንጀራውና በንጉሡ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፣ ምድሪቱም ይመታሉ፥ ከእጃቸውም አላድናቸውም።


በም​ድ​ርም ላይ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ አንድ ንጉ​ሥም በሁ​ላ​ቸው ላይ ይነ​ግ​ሣል፤ ከዚያ ወዲያ ሁለት ሕዝብ አይ​ሆ​ኑም፤ ከዚያ ወዲ​ያም ሁለት መን​ግ​ሥት ሆነው አይ​ለ​ያ​ዩም።


መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios