መዝሙር 20:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕይወትን ለመነህ፥ ሰጠኸውም፥ ለረዥም ዘመን ለዘለዓለሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልብህን መሻት ይስጥህ፤ ዕቅድህን ሁሉ ያከናውንልህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መባዎችህን ሁሉ ያስብልህ፥ የሚቃጠል መሥዋዕትህን ያለምልምልህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የልብህን ምኞት ይስጥህ፤ ሐሳብህን ሁሉ ይፈጽምልህ፤ |
እርስዋም ለንጉሡ ለሰሎሞን ካመጣችው የበለጠ፥ ንጉሡ ሰሎሞን የወደደችውን ሁሉ፥ ከእርሱም የለመነችውን ሁሉ ለሳባ ንግሥት ሰጣት፤ እርስዋም ተመልሳ ከአገልጋዮችዋ ጋር ወደ ሀገርዋ ሄደች።
እኔም ዘወትር እንደምትሰማኝ አውቃለሁ፤ ነገር ግን አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ በዚህ ቆመው ስላሉት ሰዎች ይህን እናገራለሁ።”
ያንጊዜም እኔን የምትለምኑኝ አንዳች የለም፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በስሜ አብን ብትለምኑት ሁሉን ይሰጣችኋል።
ሚስቱም፥ “እግዚአብሔርስ ሊገድለን ቢወድድ ኖሮ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ከእጃችን ባልተቀበለን፥ ይህንም ነገር ሁሉ ባላሳየን፥ እንዲህ ያለ ነገርም በዚህ ጊዜ ባላሰማን ነበር” አለችው።
አሁንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእኔን የአገልጋይህን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አስነሥቶህ እንደሆነ፥ ቍርባንህን ይቀበል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎችን አማልክት አምልክ ብለው በእግዚአብሔር ርስት ላይ እንዳልቀመጥ ዛሬ ጥለውኛልና በእግዚአብሔር ፊት ርጉማን ይሁኑ።