እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው፤ በእርሱም እታመናለሁ፤ ጋሻዬና የመድኀኒቴ ቀንድ፥ ረዳቴ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ፥ መድኀኒቴ ሆይ፥ ከግፈኛ ታድነኛለህ።
መዝሙር 18:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት ጥበብን ትናገራለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤ አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፤ እርሱ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለ፦ አቤቱ ጉልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬና አዳኜ ነው፤ አምላኬ የምጠጋበት አለቴ ነው፤ እርሱ ጋሻዬና የመዳኔ ቀን፥ ጠንካራ መመኪያም ነው። |
እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው፤ በእርሱም እታመናለሁ፤ ጋሻዬና የመድኀኒቴ ቀንድ፥ ረዳቴ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ፥ መድኀኒቴ ሆይ፥ ከግፈኛ ታድነኛለህ።
የአማልክት ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ፥ የጊደሮችን ጥጃ ለእግዚአብሔር አምጡ። ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ፥
እኔን ለማዳን ረዳትና ሰዋሪ ሆነኝ፤ ይህ አምላኬ ነው፤ አመሰግነውማለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ።
ሰውም ቃሉን ይሰውራል፤ በውኃ እንደሚጠልቅም ይሰወራል፤ ክብሩም በደረቅ ምድር እንደሚፈስስ ውኃ በጽዮን ይገለጣል።
ጌታ ሆይ! አንተ ኀይሌና ረዳቴ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ፤ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው፥ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር ለምንም የማይረባቸውን ጣዖትን ሠርተዋል” ይላሉ።