መዝሙር 16:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰኰናዬ እንዳይናወጥ አረማመዴን በመንገድህ አጽና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የርስት ድርሻዬና ጽዋዬ ነው፤ ዕጣዬም በእጅህ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው፥ ዕጣ ፈንታዬንም የምታጸና አንተ ነህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ዕድል ፈንታዬና ጽዋዬ አንተ ነህ፤ ድርሻዬንም አስተማማኝ ታደርገዋለህ። |
እነሆ፥ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ ያዕቆብ፤ ነፍሴ የተቀበለችው ምርጤ እስራኤልም፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያመጣል።
ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፤ ከኀያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ኀጢአታቸውም ተሰጠ።
የያዕቆብ ዕድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፤ እርሱ ሁሉን የፈጠረ ነውና እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነውና፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
እግዚአብሔር እርሱን ለእስራኤል ንስሓን፥ የኀጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ ራስም አዳኝም አደረገው፤ በቀኙም አስቀመጠው።
እግዚአብሔር በእኛና በእናንተ መካከል ዮርዳኖስን ድንበር አድርጎአልና በእግዚአብሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላችሁም ይሉአቸዋል፤ በዚሁም ልጆቻችሁ ልጆቻችንን እግዚአብሔርን ከማምለክ እንዳያወጡአቸው ብለን ይህን አደረግን።
ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል፥ ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቍርባን፥ በደኅንነትም መሥዋዕታችን እግዚአብሔርን እናመልክ ዘንድ፥ ነገ ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ በእግዚአብሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላችሁም እንዳይሉ ምስክር ይሆናል።