ኢያሱ 22:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል፥ ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቍርባን፥ በደኅንነትም መሥዋዕታችን እግዚአብሔርን እናመልክ ዘንድ፥ ነገ ልጆቻችሁ ልጆቻችንን፦ በእግዚአብሔር ዘንድ ዕድል ፋንታ የላችሁም እንዳይሉ ምስክር ይሆናል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 በሌላም በኩል የሚቃጠል መሥዋዕታችንን፣ ሌላውን ቍርባናችንንና የኅብረት መሥዋዕታችንን ይዘን በተቀደሰው ስፍራ እግዚአብሔርን እንደምናመልክ መሠዊያው በእኛና በእናንተ እንዲሁም በሚቀጥሉት ትውልዶች መካከል ምስክር ይሆናል። ስለዚህ ወደ ፊት ዘሮቻችሁ ዘሮቻችንን፣ ‘ከእግዚአብሔር ዘንድ ድርሻ የላችሁም’ ሊሏቸው አይችሉም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቁርባን በአንድነትም መሥዋዕታችን ጌታን እንድናገለግል፥ በሚመጣውም ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻንን፦ “በጌታ ዘንድ ድርሻ የላችሁም” እንዳይሉ ምስክር ይሆናል።’ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 እኛ እርሱን የሠራነው በእኛና በእናንተ ሕዝብ መካከል ምልክት ሆኖ እንዲኖር ነው፤ ይኸውም ከእኛ በኋላ ለሚነሡት ትውልዶች በተቀደሰ ድንኳኑ ፊት እግዚአብሔርን እንደምናመልክ የሚቃጠልና ሌላም መሥዋዕት፥ እንዲሁም የአንድነት መሥዋዕት ስናቀርብ ለመኖራችን ምስክር ይሆናል፤ ይኸውም የእናንተ ዘሮች የእኛን ልጆች ‘ከእግዚአብሔር ጋር ምንም ግንኙነት የላችሁም’ እንዳይሉአቸው ለማድረግ ይጠቅማል፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 ነገር ግን በእኛና በእናንተ መካከል ከእኛም በኋላ በትውልዳችንና በትውልዳችሁ መካከል በሚቃጠል መሥዋዕትና በቁርባን በደኅንነትም መሥዋዕታችን እግዚአብሔርን እናመልክ ዘንድ፥ በሚመጣውም ዘመን ልጆቻችሁ ልጆቻንን፦ በእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንታ የላችሁም እንዳይሉ ምስክር ይሆናል። Ver Capítulo |