ዳዊትና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣሪያዎች በበገናና በመሰንቆ፥ በከበሮና በነጋሪት፥ በጸናጽልና በዕንዚራ በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር።
መዝሙር 150:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ በጸናጽልና በእልልታ አመስግኑት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተርገብጋቢ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት፤ ድምፀ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አወድሱት፥ ድምፁ በሚሰማ ጸናጽል አወድሱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጸናጽል ድምፅ አመስግኑት፤ ከፍተኛ ድምፅ ባለው ጸናጽል አመስግኑት። |
ዳዊትና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣሪያዎች በበገናና በመሰንቆ፥ በከበሮና በነጋሪት፥ በጸናጽልና በዕንዚራ በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር።
ዳዊትና እስራኤል ሁሉ ከመዘምራን ጋር በበገና፥ በመሰንቆና በከበሮ፥ በጸናጽልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይዘምሩ ነበር።
ዳዊትም በዜማ ዕቃ፥ በመሰንቆና በበገና፥ በጸናጽልም እንዲያዜሙ፥ ድምፃቸውንም በደስታ ከፍ እንዲያደርጉ መዘምራኑን “ወንድሞቻችሁን ሹሙ” ብሎ ለሌዋውያን አለቆች ተናገረ።
እንዲሁ እስራኤል ሁሉ በይባቤ፥ ቀንደ መለከትና እንቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆም፥ በገናም እየመቱ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።
አለቃውም አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም ቀጥሎ ዘካርያስ፥ ኢያሔል፥ ሰሜራሞት፥ ይሔኤል፥ ማታትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ አብዲዶም፥ ይዒኤል በመሰንቆና በበገና፥ አሳፍም በጸናጽል ይዘምሩ ነበር።
ዳዊትና የሠራዊቱ አለቆችም ከአሳፍና ከኤማን ከኤዶትምም ልጆች በመሰንቆና በበገና፥ በጸናጽልም የሚዘምሩ ሰዎችን ለማገልገል ለዩ፤ በየአገልግሎታቸውም ሥራ የሚሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።
እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት በጸናጽልና በበገና፥ በመሰንቆም ከአባታቸው ጋራ የእግዚአብሔርን ቤት ለማገልገል ወደ ንጉሡ ቀርበው ያመሰግኑ ነበር። አሳፍም ኤዶትምም ኤማንም ያመሰግኑ ነበር።
መለከቱንም የሚነፉ መዘምራኑ በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ፥ “እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ” እያሉ በአንድ ቃል ድምፃቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው በመለከትና በጸናጽል፥ በዜማም ዕቃ ሁሉ እግዚአብሔርን ባመሰገኑ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር የክብሩ ደመና የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው።