Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 13:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዳዊ​ትና እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከመ​ዘ​ም​ራን ጋር በበ​ገና፥ በመ​ሰ​ን​ቆና በከ​በሮ፥ በጸ​ና​ጽ​ልና በመ​ለ​ከት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሙሉ ኀይ​ላ​ቸው ይዘ​ምሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሆነው በቅኔና በበገና፣ በመሰንቆና በከበሮ፣ በጸናጽልና በመለከት በሙሉ ኀይላቸው በዓሉን በደስታ ያከብሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ዳዊትና እስራኤል ሁሉ በዝማሬና በበገና በመሰንቆና በከበሮ በጸናጸልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ያሸበሽቡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ መሰንቆና በገና እየደረደሩ፥ አታሞ እየመቱ፥ ጸናጽል እያንሿሹና እምቢልታ እየነፉ በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ለእግዚአብሔር ክብር ያሸበሽቡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ዳዊትና እስራኤል ሁሉ በቅኔና በበገና በመሰንቆና በከበሮ በጸናጸልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 13:8
18 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም ባለ በገና አም​ጡ​ልኝ” አለ። ባለ በገ​ና​ውም በደ​ረ​ደረ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ መጣ።


እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤል ሁሉ በይ​ባቤ፥ ቀንደ መለ​ከ​ትና እን​ቢ​ልታ እየ​ነፉ፥ ጸና​ጽ​ልና መሰ​ን​ቆም፥ በገ​ናም እየ​መቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ካህ​ናቱ ከፍ አድ​ር​ገው ለማ​ሰ​ማት መለ​ከ​ትና ጸና​ጽል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መዝ​ሙ​ራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤ​ዶ​ታም ልጆች ግን በረ​ኞች ነበሩ።


አለ​ቃ​ውም አሳፍ ነበረ፤ ከእ​ር​ሱም ቀጥሎ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢያ​ሔል፥ ሰሜ​ራ​ሞት፥ ይሔ​ኤል፥ ማታ​ትያ፥ ኤል​ያብ፥ በና​ያስ፥ አብ​ዲ​ዶም፥ ይዒ​ኤል በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ አሳ​ፍም በጸ​ና​ጽል ይዘ​ምሩ ነበር።


አራቱ ሺህም በረ​ኞች ነበሩ፤ አራቱ ሺህም ለም​ስ​ጋና በተ​ሠ​ሩት በዜማ ዕቃ​ዎች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።


በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ፥ በመ​ለ​ከ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገቡ።


መዘ​ም​ራ​ንም የነ​በ​ሩት ሌዋ​ው​ያን ሁሉ፥ ከአ​ሳ​ፍና ከኤ​ማን፥ ከኤ​ዶ​ት​ምም ልጆች ጋር ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ ጥሩ በፍታ ለብ​ሰው ጸና​ጽ​ልና ከበሮ፥ መሰ​ን​ቆም እየ​መቱ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ በም​ሥ​ራቅ በኩል ቆመው ነበር፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር መቶ ሃያ ካህ​ናት መለ​ከት ይነፉ ነበር።


እነ​ር​ሱስ ይህን አይ​ተው አደ​ነቁ፥ ደነ​ገጡ፥ ፈሩም።


አቤቱ፥ ወን​ዞች ከፍ ከፍ አደ​ረጉ፥ ወን​ዞች ቃሎ​ቻ​ቸ​ውን ከፍ ከፍ አደ​ረጉ።


የዝ​ማ​ሬ​ህ​ንም ጩኸት ከእኔ ዘንድ አርቅ፤ የመ​ሰ​ን​ቆ​ህ​ንም ዜማ አላ​ዳ​ም​ጥም።


ከበ​ገ​ናው ድምፅ ጋር አስ​ተ​ባ​ብ​ረው ለሚ​ያ​ጨ​በ​ጭቡ ሰዎች፤ ይኸ​ውም የማ​ያ​ልፍ ለሚ​መ​ስ​ላ​ቸ​ውና እን​ደ​ሚ​ያ​መ​ል​ጣ​ቸው ለማ​ያ​ውቁ፤


ከዚ​ያም በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ ወዳ​ለ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኮረ​ብታ ትመ​ጣ​ለህ፤ በዚ​ያም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ናሴብ አለ፤ ወደ​ዚ​ያም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ በደ​ረ​ስህ ጊዜ በገ​ናና ከበሮ፥ እም​ቢ​ል​ታና መሰ​ንቆ ይዘው ትን​ቢት እየ​ተ​ና​ገሩ ከኰ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ የሚ​ወ​ርዱ የነ​ቢ​ያ​ትን ጉባኤ ታገ​ኛ​ለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos