Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 16:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አለ​ቃ​ውም አሳፍ ነበረ፤ ከእ​ር​ሱም ቀጥሎ ዘካ​ር​ያስ፥ ኢያ​ሔል፥ ሰሜ​ራ​ሞት፥ ይሔ​ኤል፥ ማታ​ትያ፥ ኤል​ያብ፥ በና​ያስ፥ አብ​ዲ​ዶም፥ ይዒ​ኤል በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ አሳ​ፍም በጸ​ና​ጽል ይዘ​ምሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከርሱ ቀጥሎ ዘካርያስ ሁለተኛ ሆኖ ተሾመ፤ ከዚያም ይዒኤል፣ ሰሚራሞት፣ ይሒኤል፣ መቲትያ፣ ኤልያብ፣ በናያስ፣ አቢዳራ፣ ይዒኤል ተሾሙ፤ እነርሱም በመሰንቆና በበገና ይዘምሩ ነበር፤ አሳፍ ደግሞ ጸናጽል የሚጸነጽል ሆኖ ተመደበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም ቀጥሎ መሰንቆና በገና ይጫወቱ የነበሩት ዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድ-ኤዶም፥ ይዒኤል ነበሩ፤ አሳፍም የጸናጽልን ድምፅ ያሰማ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አሳፍ መሪ፥ ዘካርያስም የእርሱ ረዳት ሆነው ተሾሙ፤ ይዒኤል፥ ሸሚራሞት፥ ይሒኤል፥ ማቲትያ፥ ኤሊአብ፥ በናያ፥ ዖቤድኤዶምና ይዒኤል መሰንቆና በገና ለመደርደር፥ አሳፍም ጸናጽል ለማንሿሿት ተመደቡ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አለቃው አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም በኋላ ዘካርያስ፥ ይዒኤል፥ ሰሚራሞት፥ ይሒኤል፥ መቲትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ ዖቤድኤዶምና ይዒኤል በመሰንቆና በበገና አሳፍም በጸናጽል ይዘምሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 16:5
9 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣ​ሪ​ያ​ዎች በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ፥ በከ​በ​ሮና በነ​ጋ​ሪት፥ በጸ​ና​ጽ​ልና በዕ​ን​ዚራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሙሉ ኀይ​ላ​ቸው ይጫ​ወቱ ነበር።


እን​ዲ​ሁም በየ​ቀኑ እን​ደ​ሚ​ገ​ባ​ቸው በታ​ቦቱ ፊት ዘወ​ትር ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ አሳ​ፍ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን ተዋ​ቸው።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ፊት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያወ​ድ​ሱት ዘንድ፥ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ትና ያከ​ብ​ሩ​ትም ዘንድ ከሌ​ዋ​ው​ያን ወገን አቆመ።


ካህ​ና​ቱም በና​ያ​ስና የሕ​ዜ​ኤል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ሁል​ጊዜ መለ​ከት ይነፉ ነበር።


ልጁ ተአት፥ ልጁ ኡር​ኤል፥ ልጁ ዖዝያ፥ ልጁ ሳውል።


በቀ​ኙም የሚ​ቆ​መው ወን​ድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳ​ፍም የበ​ራ​ክያ ልጅ፥ የሳ​ምዓ ልጅ፤


ይህ​ንም ትእ​ዛዝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በነ​ቢ​ያቱ እጅ አዝ​ዞ​አ​ልና እንደ ዳዊ​ትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢ​ዩም እንደ ናታን ትእ​ዛዝ፥ ጸና​ጽ​ልና በገና፥ መሰ​ን​ቆም አስ​ይዞ ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አቆመ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos